የኢትዮጵያ መንግሥት መግለጫ
ዓርብ፣ የካቲት 18 2008ማስታወቂያ
በኦሮምያ ክልል ከተከሰቱት ግጭቶች አንዳንዱ ከውጭ ድጋፍ ባላቸው መሣሪያ በታጠቁ ቡድኖች የሚካሄድ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ ። የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ትናንት ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በተለይ በምዕራብ አርሲ የሰዎች ህይወትና ንብረት የጠፋበት መሣሪያ የታጠቁ ኃይሎች ያባባሱት ግጭት ከህዝብ ጥያቄ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ተናግረዋል ። መንግሥት በየአካባቢው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስም ህብረተሰቡን እያወያየ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልፀዋል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ