1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ ሕግና ተቃዉሞዉ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 30 2001

በአዲሱ ሕግ ምክንያት ኢትዮጵያ በአመት ከስድስት መቶ ሚሊዮን እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ታጣለች።

https://p.dw.com/p/GUeY
አዲሱ ሕግ ይህን መሰሉን ችግር ያብሰዋል-ተቃዋሚዎችምስል picture-alliance/dpa

የኢትዮጵያ መንግሥት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሥራ እና አሰራር የሚገድብ ሕግ ማዉጣቱ የቀሰቀሰዉ ቁጣና ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ።ባለሙያዎችና ሕጉ የሚነካቸዉ ድርጅቶች ተጠሪዎች እንደሚሉት ሕጉ ድርጅቶቹን ብቻ ሳይሆን በድርጅቶቹ ድጋፍ የሚኖረዉን ሕዝብና ሐገሪቱን ጭምር ክፉኛ የሚጎዳ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ያነጋገራቸዉ ባለሙያዎች እንደሚሉት በአዲሱ ሕግ ምክንያት ኢትዮጵያ በአመት ከስድስት መቶ ሚሊዮን እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ታጣለች።