1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢንተርኔት ስለላ

ሐሙስ፣ መጋቢት 3 2007

የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኞችን ለመከታተል የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራሞችን መቀጠም መቀጠሉን አንድ ጥናት አመለከተ።

https://p.dw.com/p/1EpPD
Anti-Spähsoftware (Symbolbild)
ምስል Fotolia/davidevison

ዓለም ዓቀፉ የመብት ተሟጋች ሂዉመን ራይትስ ዎችና ለጋዜጠኞች መብት የሚከራከረዉ CPJ እንዳመለከቱት፤ ባለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ማለቂያ ኢትዮጵያ ይህን የመሰለያ ፕሮግራም መጠቀሟን ሲቲዝን ላብ የተሰኘዉ የካናዳ የጥናት ተቋም ይፋ አድርጓል። በጣሊያን ኩባንያ ለገበያ የቀረበዉ ይህ የኮምፕዩተር የስለላ ፕሮግራም በተለይ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ( ኢሳት) የተባለዉ ጣቢያ ጋዜጠኞች ላይ ለክትትል መዋሉ ተገልጿል።

በቶሮንቶ ካናዳ ዩኒቨርሲቲ መንክ በተሰኘዉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ተቋም የሚገኘዉ የሲትዝን ላይ ተመራማሪዎች ባለፈዉ ታህሳስ ወር መጨረሻ ገደማ ላብ ነበር ከኢሳት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከአቶ ነአምን ዘለቀ ምንነቱን እንደሚለከቱ አንድ ኤሜይል የደረሳቸዉ። እንደዘገባዉ አቶ ነአምን ስለምርጫ 2015 መረጃዎች እንደያዘ የሚጠቁመዉን የኢሜይል መልዕክት ዉስጡን በመጠራጠር ነበር የፀጥታ፤ የሰብዓዊ መብቶችና የመረጃ ቴክኒዎሎጂን በሚመለከት ለሚመራመረዉ ቡድን ያስተላለፉት። ብዙም ሳይቆይ ሲቲዚን ላብ ያ መልዕክት በመንግሥት የሚተዳደረዉ የኢትዮ ቴሌኮም የኮምፕዩተር ማዕከል ጋ የተገናኘ መሆኑን እንደረሰበት ይገልጻል። የሂዉመን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ ፊሊክስ ሆርን፤

Symbolbild Computer Hacker
ምስል Reuters/Dado Ruvic

«የሲቲዝን ላብ ተመራማሪዎች በርካት ተመሳሳይ ጉዳዮችን አግኝተዋል። ከኢሳት ጋ ግንኙነት ያላቸዉ በዉጭ የሚገኙ ጋዜጠኞች ለመንግሥታት ሰላይ የኮምፕዩተር ፕሮግራም በሚያቀርበዉ በጣሊያን ኩባንያ የስለላ ፕሮግራም በየግላቸዉ ጥቃት እንደደረሰባቸዉ አረጋግጠዋል። አንድ ኮምፕዩተር አንዴ በዚያ ሰላይ ፕሮግራም ከተጠመደ ኮምፕዩተሩን ያጠመደዉ ግለሰብ የፈለገዉን መረጃዎችን ማግኘት ይችላል። የኢሜል፤ የስካይፕ ግንኙነቶችን ና አድራሻዎችን ማግኘት ይችላል፤ ባለቤቱ ሳያዉቅ የዌብ ካሜራዉን ሊከፍት ይችላል፤ ባጠቃላይ የዚያን ሰዉ ኮምፕዩተርን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠረዋል።»

ይላሉ። ከዚህ ቀደም በጎርጎሪዮሳዊዉ የዘመን ቀመር 2013 ዓ,ም ላይ ሂዉማን ራይትስ ዎችና ሌሎች ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሥት በዉጭ ሃገር የሚገኙ ጋዜጠኞችን ኮምፕዩተሮች ለማጥመድ የስለላ ፕሮግራም እንደሚጠቀም አመልክተዉ ነበር። ድርጊቱ አሁንም መቀጠሉ ፊሊክስ ሆርን እንደሚሉት እንዲህ ያለዉን የኮምፕዩተር የስለላ ፕሮግራም የሚያመርቱት ኩባንያዎች የሚሸጡላቸዉ መንግሥታት ለምን ተግባር እንዳዋሉት መከታተልና ተገቢዉን እርማት ማድረግ አለመፈለጋቸዉን ያሳያል።

Symbolbild China Hackerangriff auf US Firmen 20.05.2014
ምስል Reuters

በቅርቡ ኮምፕዩተራቸዉን ሊያጠምዱ ተሞክሯል ወደተባለዉ የኢሳት ጋዜጠኖች የተላኩ መልዕክቶች የግንቦት ሰባት አመራር ስለሆኑትና ኢትዮጵያ ዉስጥ በእስር ላይ ስለሚገኙት አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የሚገልፅ አባሪ መልዕክትና ሌሎችም ተያያዥ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የያዙ እንደሚመስሉ ነዉ ፊሊክስ ሆርን አረጋግጠዋል። ለምን ይሆን በዚህ ወቅት የኢሳት ጋዜጠኞች የሚጠረጠረዉ የመንግሥት የኢንተርኔት ስለላ ኢላማ ሊሆኑ የቻሉት? ፊሊክስ ሆርን፤

«ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ዉስጥ ስንመለከት በተለያዩ መንገዶች የግል መገናኝ ብዙሃንን መንግሥት እያዋከበ ነዉ። ማስፈራራት፤ ማዋከብ በመኖሩም ወደ30 የሚሆኑ ጋዜጠኞች በ2014 ከኢትዮጵያ ተሰደዋል። እናም ይህ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባሉት ላይ ሳይሆን ከመንግሥት የቅርብ ክትትል ራቅ በሚሉት ላይ ነዉ። ስለዚህ በዚህ የኮምፕዩተር ስለላ ፕሮግራም አማካኝነትም መንግሥት ስለኢትዮጵያ ጉዳይ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ኮምፕዩተር ዉስጥ ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ፤ እንዲሁም ደግሞ ለእነዚህ ጋዜጠኞች ማለትም ለኢሳት የመረጃ ምንጮች እነማን እንደሆኑ ለማጣራት ይጠቀምበታል። በቅርቡ ይፋ ባደረግነዉ ዘገባም ኢትዮጵያ ዉስጥ ለኢሳትም ሆነ ለሌሎች የዉጭ ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙሃን መረጃ በመስጠት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ዒላማ ሆነዋል።»

Antenne für Satellitenkommunikation
ምስል DW/C. Dillon

የጣሊያን ኩባንያ የሆነ የሃኪንግ ቲም ምርቶችንም ሆነ የጀርመኑን ኩባንያ የፊን ፊሸርን የኢንተርኔት የስለላ ፕሮግራሞች የተለያዩ መንግሥታት ለየግል ጉዳዮቻቸዉ እንደሚጠቀሙባቸዉ ነዉ የሂዉማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ ያስረዳሉ። በተለይ ግን ይህ አሁን በኢትዮጵያ መንግሥት ዉጭ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ለመሰለል ዉሏል የተባለዉ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ናይጀሪያ ና ባህሬንን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት መንግሥታት እንደሚጠቀሙበት ታይቷል። በሕጋዊ መንገድ ሥራ ላይ የሚዉለዉም ወንጀልና የሽብር ተግባራትን ለመከታተል ነዉ። ከዚህ አልፎ ግለሰብ ጋዜጠኞችን በዚህ ለመከታተል መሞከት አግባብ አለመሆኑን ያመለከቱት ፊሊክስ ሆርን ኩባንያዎቹ ራሳቸዉም ኃላፊነት እንዳለባቸዉ ይገልጻሉ።

«በመሠረቱ ኩባንያዎቹ ራሳቸዉ መንግሥታት የእነሱን ምርት አላግባብ ለሚጠቀሙበት መንግሥታት ያለመሸጥ ኃላፊነት አለባቸዉ። ለኩባንያዎቹም ምርቶቻቸዉ በምን ተግባር እንደዋሉ ለማጣራት አዳጋች አይሆንም። የሃኪንግ ቲምና የኢሳትን ጉዳይ ስንመለከት፤ በሂዉማን ራይትስ እና በሲቲዚን ላብ የመጀመሪያ ዘገባዎች አማካኝነት ምርታቸዉ በኢትዮጵያ መንግሥት የግል ጋዜጠኞችን ለመሰለል እንደዋለ መረጃ ቀርቦላቸዋል። ይህም ሃኪንግ ቲም ጉዳዩን መርምሮ ምርቱ ለዚህ ተግባር መዋል እንደሌለበት ማሳወቅ ነበረበት። የአሁን አጋጣሚም የሚያመለክተዉ ኩባንያዉ ምንም ያደረገዉ ለዉጥ ሳይኖር በንግዱ መቀጠሉን ነዉ።»

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ