1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫና ሑዩማን ራይትስ ዋች

ማክሰኞ፣ ግንቦት 17 2002

እስከ ድምፅ መስጪያዉ ዕለት ድረስ በነበረዉ የምርጫ ሒደት ሕዝቡ ነፃ ሆኖ ድምፁን እንዳይሰጥ ገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ጫና ሲያደርግበት ነበር

https://p.dw.com/p/NWNZ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ እሁድ የተደረገዉ አጠቃላይ ምርጫ ነፃ እንዳይሆን የሐገሪቱ ገዢ ፓርቲ ከፍተኛ ተፅዕኖ አድርጎበታል ሲል አለም አቀፉ የሠብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሑዩማን ራይትስ ዋች ከሰሰ።መንበሩን ኒዮርክ-ዩናይትድ ስቴትስ ያደረገዉ የመብት ተማጋች ድርጅት እንደሚለዉ የእሁዱ ድምፅ አሰጣጥ ሠላማዊ ነበር።ይሁንና ድርጅቱ አክሎ እንዳለዉ እስከ ድምፅ መስጪያዉ ዕለት ድረስ በነበረዉ የምርጫ ሒደት ሕዝቡ ነፃ ሆኖ ድምፁን እንዳይሰጥ ገዢዉ ፓርቲ ከፍተኛ ጫና ሲያደርግበት ነበር።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ