1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ ሕግ፥ ገዢዉ ፓርቲና ተቃዋሚዎች

ሐሙስ፣ ጥቅምት 19 2002

የኢትዮጵያ ገዢ የፖለቲካ ማሕበር ኢሕአዴግና አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተስማሙበት የምርጫ ደንብ በቅርቡ ለሐገሪቱ ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ የመገናኛ ብዙሐን ጉዳይ ሚንስትር አቶ በረከት ሥምኦን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/KIew
ምስል AP

አቶ በረከት ዛሬ ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ እንዳሉት ሕጉን ሁሉም የፖለቲካ ማሕበር የማክበር ግዴታ አለበት።እስካሁን ዉሉን ያልተቀበሉ ግን ወደፊት የመቀበል መብታቸዉ የተጠበቀ ነዉ።አቶ በረከት ከምርጫ ሌላ ኢትዮጵያን ሥለሚያሰጋዉ ረሐብ፥ ሥለ መልካም አስተዳደርና ሰብአዊ መብት ይዞታም ማብራሪያ ሰጥተዋል።ታደሰ እንግዳዉ ጋዜጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎት ነበር።


ታደሰ እንግዳዉ/ነጋሽ መሀመድ/አርያም ተክሌ