1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ አወዛጋቢ ዉጤት፥ እና የሐገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት

ሰኞ፣ ሰኔ 21 2002

የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት፥ የፍርድ ቤቶች አወቃቀር ግን ቢያንስ ለባለሙያ እንግዳ አይደለም

https://p.dw.com/p/O57M
Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Erklärung der Wahlprozedur in Oromia, Äthiopien 23.Mai 2010 Thema: bei Äthiopiens Parlamentswahl 2010 erklärt dieser Wahlhelfer Wählern in Debre Zeit, Oromia, die Wahlprozedur Schlagwörter:Wahl Äthiopien 2010, Stimmabgabe, Polls, Voting Ethiopia 2010ምስል DW

28 06 10

የኢትዮጵያ ምርጫ አወዛጋቢ ዉጤት፥ የፍርድ ቤቱ ሙግት እና የሐገሪቱ የፍትሕ ሥርዓት።ባለፈዉ ግንቦት 15 የተደረገዉን ምርጫ አወዛጋቢ ዉጤትን አስታከን ዛሬም እንደገና ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ እንላለን ላፍታ አብራችሁን ቆዩ። ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ናቸዉ።የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳትና ያሁኑ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ-ባለፈዉ ሳምንት ሰኞ።

እሳቸዉ ደግሞ አቶ ያቆብ ልኬ ናቸዉ።የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ።-እንደገና ባለፈዉ ሳምንት።በክስ ሙግቱ የሚሔዱበት ርቀት እስከየትነት በርግጥ አይታወቅም።የኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት፥ የፍርድ ቤቶች አወቃቀር ግን ቢያንስ ለባለሙያ እንግዳ አይደለም።

ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻ።ዛሬ በርግጥ ስደተኛ ናቸዉ።1997ቱ ምርጫ ዉጤት ዉዝግብ-ግጭት ግድያ መዘዝ ካገር እስካሰደዳቸዉ ድረስ ግን-በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ያገለገሉ ዳኛ፣ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት፥ የአጣሪ ኮሚሽን ምክትል ሰብሳቢም ነበሩ።ዳኛ ወልደሚካኤል ዛሬም ከስደት ግን ሥለ-ምርጫና ዉዝግቡ ይነጋራሉ።ስላሰደዳቸዉ ሳይሆን ሥለ ዘንድሮዉ ምርጫ።ዛሬም ሥለ ኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ይናገራሉ።እንቀጥል።

ዳኛ ወልደ ሚካኤል መሸሻን አመሰግናለሁ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

ነጋሽ መሐመድ