1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ ዉጤትና ጠሚ መለስ

ሐሙስ፣ ግንቦት 19 2002

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ፓርቲያቸዉ ሙሉ በሙሉ ያሸነፈበት ምርጫ እንዲደገም ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያቀረቡትን ጥያቄ እንደማይቀበሉት አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/NYnz
ጠ/ሚር መለስ ዜናዊምስል AP

ጠቅላይ ሚንስትሩ «ከሕግ ያለፈ» ያሉትን እርምጃ ተቃዋሚዎቻቸዉ እንዳይወስዱም አስጠነቀቁ።ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ትናንት ማምሻ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አክለዉ እንዳሉት ምርጫዉን በተመለተከተ መንግሥታቸዉ ከዉጪ የሚደረግበትን ግፊት አይቀበለዉምም።ጋዜጣዊ መግለጫዉን ታደሰ እንግዳዉ ተከታትሎት ነበር።  ታደሰ እንግዳዉ ነጋሽ መሀመድ አርያም ተክሌ