የኢትዮጵያ ምርጫ ዉጤት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2005ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ ሚዚያ መጀመሪያ እና አጋማሽ ላይ የተደረገዉ የአካባቢና የከተሞች መስተዳድሮች ምርጫ ዉጤት በተያዘለት ጊዜ የፊታችን አርብ ይፋ እንደሚሆን የሐገሪቱ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።የቦርዱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ቦርዱ በያዘዉ የጊዜ ሠሌዳ ዉጤቱን ለማሳወቅ የሚያስፈልጉትን መረጃዎች በሙሉ አሰባስቧል። በዘንድሮዉ ምርጫ ያልተካፈሉትን የአብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ቅሬታና ጥያቄም ቦርዱ ወደፊት የሚመለከተዉ መሆኑን አቶ ይስማዉ ገልፀዋል።አቶ ይስማዉን በስልክ አነጋግሬቸዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ