የኢትዮጵያ ምርጫ ውጤትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 16 2007የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ግንቦት 16 2007 ዓ,ም የተካሄደዉን ምርጫ የመጨረሻ ዉጤት ትናንት ከቀትር በኋላ ይፋ ካደረገ በኋላ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች የምርጫ ሂደቱ የተጭበረበረ ስለነበር ዉጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል የታወቀ እንደነበር ተናግረዋል። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት፤ ምርጫ ነበረና ምርጫ ተደረገ የሚያሰኝ ነገር አልነበረም ነዉ ያሉት። እንድያም ሆኖ አሁን መድብለ ፓርቲ አበቃለት ማለት አይቻልም ብለዋል። ምክንያቱም መድብለ ፓርቲ የሚያበቃለትም ሆነ የሚመሰረተዉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ነዉ። በይፋዊ ዉጤቱ የገዥዉ ፓርቲ ወዳጆች ብቻ ሳይሆኑ ራሱ ገዥዉ ፓርቲም ተደናግጦበታል፤ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት አንድነት በአጭሩ ምክትል ሊቀመንበርና የፓርቲዉ የዉጭ ጉዳይ ኃላፊ ዶክተር መረራ ጉዲና በበኩላቸዉ የምርጫዉ ዉጤት በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ሊታሰብ የማይችል ሲሉ ነዉ የገለፁት።
በአቶ ትዕግስቱ አወሉ የሚመራዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ደግሞ «ኢ ሕ አ ዴ ግ» መቶ በመቶ ማሸነፉ የተነገረን የምርጫ ዉጤት በሂደቱ ብዜ ችግሮች ነበሩት ፤ በቶ በመቶ የሚለዉ ነገር በግሌ የማላምንበት ነዉ ፤ ፓርቲዉ ግን በቅርቡ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ