1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ ይፋ ዉጤት፥ ዉዝግቡና ክሱ

ሰኞ፣ ሰኔ 14 2002

አስር ሰአት ላይ ግን ዉጤቱ አልተነገረም።ምክንያቱ፥- የአለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ የቴሌቪዥን ሥርጭት እስከሚጠናቀቅ የሚል ነዉ።

https://p.dw.com/p/NzPk
ምርጫምስል DW

21 06 10

ዛሬም እንደገና ባለፈዉ ግንቦት አስራ-አምስት ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉን ምርጫ አስታከን ዉጤቱን፥ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋምና የፍርድ ቤት ሙግትን አንስተን የሁለት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናትንና የአዲስ አበባ ወኪላችንንን አነጋግረናል።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈዉ ግንቦት አስራ-አምስት የተደረገዉን ምርጫ የመጨረሻ ዉጤት ዛሬ-ረፈዱ ላይ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ነበር።አላደረገም።ተዛዋረ።ምክንያት፣- የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደነገረን-ምክንያት አልተሰጠም።
የምርጫዉ የመጨረሻ ዉጤት ምንም ሆነ-ምን ስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያስተናብረዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ባለሥልጣናት እንዳሉት ፓርቲያቸዉ የሚጠብቀዉ ነገር የለም።የመድረክ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢና የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ እንዳሉት ፓርቲያቸዉ በፍርድ ቤቱ ሙግት ይቀጥላል።

እንደ መድረክ ሁሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን የከሰሰዉ የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ከሚለዉ ዉጤት የሚጠብቀዉ የለም።የድርጅቱ የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ያዕቆብ ልኬ ፓርቲያቸዉ ይሕን አቋም ለመያዙ ብዙ ምክንያት ይዘረዝራሉ።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻዉን ዉጤት ለማስታወቅ ለዛሬ ጧት አምስት ሰአት ይዞት ሰጥቶት የነበረዉን ቀጠሮ የቀየረዉ ወደ አስር-ሰአት ነበር።አስር ሰአት ላይ ግን ዉጤቱ አልተነገረም።ምክንያቱ፥- የአለም የእግር ኳስ የዋንጫ ግጥሚያ የቴሌቪዥን ሥርጭት እስከሚጠናቀቅ የሚል ነዉ።

Dr. Negasso Gidada
ዶ/ር ነጋሶምስል DW

ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ