1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ መግለጫ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2005

አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ለመሳተፍ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ቢያስቀምጡም የራዕይ ፓርቲ ግን በምርጫው ለመሳተፍ መወሰኑን አስታውቀዋል ። መሪዎቹ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሮችን መሾሙን ህገ መንግሥቱን የጣሰ በማለት ተቃውመዋል

https://p.dw.com/p/179Dj
ምስል DW

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ በመጪው ሚያዚያ በሚካሄደው የአዲስ አበባና የአካባቢ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታወቀ ። የፓርቲው መሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው ለመሳተፍ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ቢያስቀምጡም የራዕይ ፓርቲ ግን በምርጫው ለመሳተፍ መወሰኑን አስታውቀዋል ። መሪዎቹ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ሁለት ተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሮችን መሾሙን ህገ መንግሥቱን የጣሰ በማለት ሲቃወሙት በየአካባቢው መስተዳደር የተለያዩ ምክንያቶች በመስጠት ቤቶች መፍረሳቸውን የዜግነትን መብት መጣስ ነው በማለት አውግዘውታል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር

ሒሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ