1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ስሞታ

ዓርብ፣ ነሐሴ 1 2007

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በታጣቂዎች ተደብድበው ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን አባሉን በእማኝነት በአካል አቅርቦ አሳይቷል

https://p.dw.com/p/1GBcD
Äthiopien Pressekonferenz Raei Partei
ምስል DW/Y. G. Egziabher

[No title]


የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ከግንቦቱ ምርጫ በኋላም በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አባላቶቼ እየታሰሩና እየተደበደቡ ነው ሲል ስሞታ አቀረበ። ፓርቲው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን እንዲሁም በደቡብና በአማራ ክልሎች አባላቶቹ ላይ ተፈፀሙ ያላቸውን በደሎች ዘርዝሯል ።በዚሁ መግለጫ ላይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በታጣቂዎች ተደብድበው ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን አባሉን በእማኝነት በአካል አቅርቦ አሳይቷል ።የፓርቲው ሃላፊዎች የሰጡትን መግለጫ የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ