1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ይዞታና የለንደኑ ስብሰባ

ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2001

አዉሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የመብት ተሟጋቾች፥ የሲቢል ማሕበረሰብ ተወካዮችና አዋቂዎች የብሪታንያ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠዉን ርዳታ እንዲያቆም ጠይቀዋል

https://p.dw.com/p/IQOJ
የብርታንያ ምክር ቤትምስል AP

በአደጊ ሐገራት ሰብአዊ መብት እንዲከበር የሚታገለዉ «ትብብር ለሰሰወስተኛዉ አለም ሰላም፥ ፍትሕና ዴሞክራሲ» የተሰኘዉ አለም አቀፍ ተቋም ሥለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ይዞታ ለመነጋገር ያዘጋጀዉ የአንድ ቀን ዉይይት ትናንት ለንደን-ብሪታንያ ዉስጥ ተደርጓል።በብሪታንያ ምክር ቤት አዳራሽ በተደረገዉ ስብሰባ ላይ አዉሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የመብት ተሟጋቾች፥ የሲቢል ማሕበረሰብ ተወካዮችና አዋቂዎች የብሪታንያ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት የሚሰጠዉን ርዳታ እንዲያቆም ጠይቀዋል።በስብሰባዉ ላይ የብሪታንያ የምክር ቤት ተወካዮችና የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎችም ተካፋዮች ነበሩ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝረ ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነሕ/ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ