1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ

ረቡዕ፣ ጥር 27 2007

በአሁኑ የዓየር ሰዓት ድልድል ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ ባለፈው ምርጫ ከነበረው የዓየር ሰዓት ያነሰ እንደሚያገኝ ተገልጿል ።

https://p.dw.com/p/1EVPq
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ምስል DW


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎችን የምዝገባ ጊዜ መራዘሙን አስታውቋል ። ቦርዱ ትናንት እንዳለው ዛሬ ያበቃየነበረው የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ በአንድ ሳምንት እንዲራዘም ተደርጓል በምርጫው ለሚሳተፉ ፓርቲዎች የምርጫ ዘመቻ የሚያካሂዱበት የአየር ሰዓት ድልድልም አውጥቷል ። በአሁኑ የዓየር ሰዓት ድልድል ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ ባለፈው ምርጫ ከነበረው የዓየር ሰዓት ያነሰ እንደሚያገኝ ተገልጿል ።በምርጫ ቦርድ ውሳኔዎች ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላን ያነጋገረውን የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔርን በስልክ አነጋግረነዋል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ