1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ተቃውሞና የአሜሪካ ምላሽ

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 2 2008

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ በሰላማዊ ሰልፍ እና የአቤቱታ ፊርማ በማሰባሰብ የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ መስተዳድር በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያሳድር በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/1JxIK
Logo USA Außenministerium State Department
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

የኢትዮጵያ መንግሥት በዜጎቹ ላይ ግድያ፤እስራት፤ እና የመብት ረገጣ ቢያደርሰም የኦባማ መስተዳድር እስካሁን ሁነኛ እርምጃ መዉሰድ አልፈለገም።በዚሕም ምክንያት የኦባማ መስተዳድር በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ለስላሳ ዲፕሎማሲ ይከተላል እየተባለ ይተቻል። ባለፈው ሳምንት ለጉብኝት ወደ ጁባ ያቀኑት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ ከልክ ያለፈ ኃይል ተጠቅሟል ሲሉ ተችተዋል። በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ «በጣም አስጊ» ያሉት አምባሳደሯ መንግስት ዜጎች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ መጠየቃቸውን ተናግረው ነበር። ዋሽንግተን የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ዘጋቢ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትን አነጋግሮዋል።
መክብብ ሸዋ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ