1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አትሌቶች ማጣሪያ

ረቡዕ፣ ሰኔ 22 2008

በርካታ ወጣት እና ታዋቂ አትሌቶች በሚሳተፉበት በዛሬው ውድድር በቅርቡ በሪዮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን ከሚወከለው ቡድን ውጭ የሆነው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ይካፈላል ።

https://p.dw.com/p/1JFqq
Äthiopien Kenenisa Bekele
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

በሪዮ ደጀኔሮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን ወክለው በተለያዩ ርቀቶች የሚወዳደሩ አትሌቶች ምርጫ እየተካሄደ ነው ። ኢትዮጵያውያን ውጤታማ በሆኑበት በ10 ሺህ ሜትር ርቀት በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ማንነት ዛሬ ምሽት በኔዘርላንድስ ሄንግሎ ከተማ በሚደረገው የማጣሪያ ውድድር ይለያል ። በርካታ ወጣት እና ታዋቂ አትሌቶች በሚሳተፉበት በዛሬው ውድድር በቅርቡ በሪዮው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በማራቶን ከሚወከለው ቡድን ውጭ የሆነው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ይካፈላል ። ቀነኒሳ ዛሬ በጥሩ ሰዓት ውድድሩን ከጨረሰ በሪዮው ኦሎምፒክ በማራቶን ለመካፈል ያጣውን እድል በ10 ሺህ ሜትር ያሳካል ተብሎ ይጠበቃል ። ከሴቶች አትሌት መሠረት ደፋር ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም ከውድድር ውጭ መሆንዋ ተገልጿል ። የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝር ዘገባ አላት ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ