1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አዉሮፕላን የአደጋ መንስኤ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 9 2005

ባለፈዉ ሳምንት በለንደን ሂትሮ አዉሮፕላን ማረፍያ እንደቆመ የእሣት ጢስ የታየበት ኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ቦይንግ 787 ድሪምላይነር ለእሳት የተጋለጠበት ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።

https://p.dw.com/p/198jS
Emergency crew surrounds a Boeing 787 Dreamliner, operated by Ethiopian Airlines, which caught fire at Britain's Heathrow airport in this July 12, 2013 still image taken from video. The plane caught fire at the airport on Friday, forcing the closure of both runways. Television footage showed the Dreamliner surrounded by foam used by firefighters. Heathrow briefly closed both its runways to deal with the fire which broke out while the plane was parked at a remote stand. There were no passengers aboard the plane. REUTERS/Pool via Reuters TV (BRITAIN - Tags: TRANSPORT DISASTER TPX IMAGES OF THE DAY) ATTENTION EDITORS - NO ACCESS UK/DAYBREAK. NO SALES. NO ARCHIVES. FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. UNITED KINGDOM OUT. NO COMMERCIAL OR EDITORIAL SALES IN UNITED KINGDOM
ምስል Reuters

የብሪታንያዉ የሲቪላቬሽን የአደጋ መርማሪ ተቋም  የአይን ምስክሮችን እና በአዉሮፕላኑ ላይ የተገኙ መረጃዎችን ጠቅሶ ጢሱ የተከሰተዉ በሞተሩ ከፍተኛ ግለት  በመፈጠሩ እንደሆነ አስታዉቆአል።

Äthiopien ist nach Japan das zweite Land, an das der neue Boeing-Flagschiff "Dreamliner" ausgeliefert wird. Copyright: Getachew Tedla/DW, 19.08.2012, Addis Abeba, Äthiopien
ምስል DW/Tedla Getachew

ባለፈዉ  አርብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 787 ድሪምላይነር የመንገደኞች ማመላለሻ አዉሮፕላን  በለንደኑ ሂትሮው አየር ጣቢያ አንድም ተሳፋሪ በሌለበት እና በቆመበት የታየዉ ጢስ እንደተጠበቀዉ በቀጥታ የባትሪ ችግር እንዳልሆነ እየተነገረ ነዉ። የቃጠሎዉ ትክክለኛ መንስኤ ግን አልታወቀም። የብሪታንያዉ የሲቪላቬሽን የአየር አደጋ መርማሪ ተቋም ባወጣዉ መግለጫ ከቀኑ 9: 50ላይ የተነሳዉ ጢስ ምስክሮች በሰጡት ቃል እና በአዉሮፕላኑ አካል ላይ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እሳቱ የተነሳዉ በላይኛዉ ወይም ስተኋላ ላይ ባሉት ሞተሮች በተፈጠረ ግለት ነዉ።  የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቃጠሎዉን  መንስዔ ገና እየተጣራ መሆኑን አስታዉቆአል። የአየር መንገዱ የበረራ ኦፕሪሽን ኋላፊ ካቲቴን ደስታ ዘርኡም ይህንኑ ነዉ የገለጹልን።

በብሪታንያ ሲቪላቬሽን መርማሪ ተቋም ከባድ ያለዉ አደጋ መንስኤ በጥንቃቄ እየመረመረ መሆኑን አስታዉቆአል። ተቋሙ ምርመራዉን ትኩረት ሰቶ የሚከታተለዉ ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ለመከላከል ነዉ ይላል።  በብሪታንያ ሲቪላቬሽን የአየር አደጋ መርማሪ ተቋምም  የአደጋዉን መንስኤ ለማጣራት ቴክኒካዊ ምርመራዉ ጀምሮአል። አዉሮፕላኑ በአሁኑ ወቅት በለንደን ሂትሮ አየር ማረፍያ መጠለያ ቦታ መቆሙንና የአዉሮፕላኑ የላይኛዉ አካል እስከ መጨረሻዉ ሞተር ድረስ መቃጠሉን የመርማሪ ተቋሙ ጋዜጣዊ መግለጫዉ ያትታል። የአዉሮፕላኑ ዉስብስብ ክፍሎች በመጎዳታቸዉ የምርመራዉ ሂደት ግዜ ሳይፈጅ እንደማይቀር ተያይዞ ተጠቅሶአል። እንድያም ሆኖ ሌሎቹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787 ድሪምላይነር የመንገደኛ ማጓጓዣ አዉሮፕላኖች በረራቸዉን መቀጠላቸዉ ካፒቴን ደስታ ዘርኡ ገልጸዉልናልድሪምላይነር የተሰኘዉ አሜሪካ ሰራሽ አዉሮፕላን ከዚህ ቀደም የባትሪ ችግር አጋጥሞት በመላዉ ዓለም የሚገኙ ድሪምላይነር ቀዉሮፕላኖች እንዳይንቀሳቀሱ መታገዳቸዉ የሚታወስ ነዉ።

An Ethiopian Airlines' 787 Dreamliner takes-off from the Bole International Airport in Ethiopia’s capital Addis Ababa, April 27, 2013. Ethiopian Airlines on Saturday became the world's first carrier to resume flying Boeing Co's 787 Dreamliner passenger jets, landing the first commercial flight since the global fleet was grounded three months ago following incidents of overheating in the batteries providing auxiliary power. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: BUSINESS TRANSPORT)
ምስል Reuters

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ