1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድና ቱሪዝም

ማክሰኞ፣ ግንቦት 12 2006

የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት መስሪያ ቤታቸዉ ኢትዮጵያን ለሐገር ጎብኚዎች ማራኪ ለማድረግ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ይሠራል።

https://p.dw.com/p/1C3H0
ምስል Reuters

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢትጵያን የተለያዩ አካባቢዎች ለመጎብኝት ለሚፈልጉ ሐገር ጎብኚዎች ከአዉሮፕላን የበረራ ቲኬት እስከ አርባ በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።የአየር መንገዱ ባለሥልጣናት እንደሚሉት መስሪያ ቤታቸዉ ኢትዮጵያን ለሐገር ጎብኚዎች ማራኪ ለማድረግ ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ ድርጅቶች ጋር ተባብሮ ይሠራል።ለሐገር ዉስጥ በረራ በ በቲኬት ዋጋ ላይ የተደረገዉ ቅናሽም ከሚያዚያ መጨረሻ ጀምሮ ገቢራዊ ሆኗል።የኢትዮጵያ የቱሪዝም መሥሪያ ቤትም ለሐገር ጎብኚዎች ሳቢ የሆኑ አካባቢዎችን፤ ቅርሶችንና ተቋማትን በጥንቃቄ ለመያዝና ለማስተዋወቅ እንደሚጥር የመስሪያ ቤቱ ሐላፊዎች አስታዉቀዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ