1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስተባበያ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 29 2002

ባለፈው ጥር 17 ,2002 ዓ.ም ሜዲትራንያን ባህር ውስጥ የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስኤ የፓይለት ስህተት እንደሆነ ተደርጎ ሰሞኑን በድጋሚ የቀረበው ዘገባ እንደ በፊቱ ሁሉ ከዕውነት የራቀ ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ ።

https://p.dw.com/p/NIrc
ምስል AP

ስለዘገባው ዶይቼቬለ ያነጋገራቸው የአየር መንገዱ የበረራ መምሪያ ሀላፊ ካፕቴን ደስታ ዘሩ ዜና አገልግሎቱ ስለ አብራሪዎቹ የበረራ ልምድ ያሰራጨውን ዜናም ፣ ሐሰት ሲሉ አስተባብለዋል ። በሌላም በኩል በአውሮፕላን አደጋው የሞቱ ተሳፋሪዎች ቤተሰቦችን በመወከል ከቦይንግ መረጃ የጠየቀው ኮሬይን ቲለሪ የተሰኘው የህግ አማካሪ ድርጅት መልሱን በመጠባበቅ ላይ መሆኑን በኢትዮጵያ የህግ አማካሪው ተጠሪ ተናግረዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ