1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራሩ

ሰኞ፣ መስከረም 22 2010

የአየር መንገዱ ዋ/ሥራ አስፈጻሚ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻውን የወረቀት ሰነድ ፈርመው ያገለገሉ ወረቀቶችን በማቃጠል ወደ ኤሌክትሮኒክ የተቀየረውን የአሰራር ሽግግር ይፋ አድርገዋል። ዋ/ሥራ አስፈጻሚው አቶ ተወልደ ገ/ማርያም አየር መንገዳቸው ላለፉት 10 አመታት ወረቀትን ከግልጋሎት ውጪ ለማድረግ መጣሩን በጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/2l7eU
Äthiopien Airlines
ምስል DW/T.Hailegiorgis

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ አደረገ

 

ከአሁን በኋላ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና፤ የበረራ፤ የንግድ የፋይናንስ፤ የሰው ሐይል አስተዳደር፤ የደንበኞች አገልግሎት የግዢ አቅርቦት ሥራዎች በሙሉ በኤሌክትሮኒክ የሚከወኑ ይሆናል። አቶ ተወልደ እንደተናገሩት ባለፉት አምስት አመታት ኩባንያቸው የአሰራር ሽግግር ለማድረግ በኢንፎርሜሽን ኮምዩንኬሽን ቴክኖሎጂው ዘርፍ የ50 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን ገልጠዋል። ሽግግሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በወጪ ቁጠባ እና የአሰራር ቅልጥፍናን በማሳደግ  ውጤታማ ያደርገዋል ተብሏል። ካሁን በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደንበኞች የጉዞ ቲኬቶቻቸውን በድረ-ገፅ መቁረጥ ይችላሉ። አየር መንገዱ ደንበኞቹ በተንቀሳቃሽ ስልክ በሚቀርበው የባንክ አገልግሎት አማካኝነት ክፍያ መፈጸም እንዲችሉ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ዳሸን ባንክ እና ኅብረት ባንክ ጋር ሥምምነት ፈፅሟል። 

Äthiopien Airlines
ምስል DW/T.Hailegiorgis

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ