1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት ማከማቻ ሕንፃ ግንባታ

ሰኞ፣ የካቲት 16 2007

ከጊዜ ወደጊዜ ዕድገት እያሳየ እንደመጣ የሚነገርለት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ ፣ ሁለት አዳዲስ የአይሮፕላን ጭነት (ካርጎ) ማከማቻ ሕንጻዎችን መገንባት መጀመሩ ተገለጠ።

https://p.dw.com/p/1EgAs
ምስል Reuters

የሕንጻ ገንቢው ተቋራጭ በኢትዮጵ የሚገኝ የአንድ የኢጣልያ ኩባንያ ሲሆን፤ ግንባታው የሚካሄደውና በውስጡ ለሚገኙ ቁሳቁሶች አቅርቦት በፈረንሳይና ጀርመን ከሚገኙ ባንኮች ብድር የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። በሁለት ፈረቃ የሚሠሩት ሕንጻዎች፣ በዓመት ከአንድ ሚሊዮ ን 200ሺ ቶን በላይ የጭነት ቁሳቁስ የሚከማችበትና በየበረራ አቅጣጫዎቹ አገልግሎት የሚያበረክት ይሆናል። የአይሮፕላን ጭነት ማከማቻው ሕንጻ በግዙፍነቱ በአፍሪቃ የመጀመሪያው ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃም ከታላላቆቹ አንዱ ሊባል እንደሚችል ተብራርቷል ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ