1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ መጻዔ-ዕድል

እሑድ፣ የካቲት 2 2006

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከአንድ ዓመት ገደማ በፊት፤ ከምድቡ ማጣሪያ ውድድሮችን አሸንፎ በአፍሪቃ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ፤ ከ 31 ዓመታት ጥረት በኋላ ለመሳተፍ መብቃቱ ፤

https://p.dw.com/p/1B5Zy
ምስል DW/H. Turuneh

ባይሳካለትም ፤ ዘንድሮ በብራዚል በሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ አፍሪቃን ከሚወክሉት 5 ቡድኖች መካከል አንዱ ሆኖ ለመገኘት ከተወዳደሩት 10 የአፍሪቃ ቡድኖች አንዱ ነው።
ቡድኑ ከዚህ ደረጃ እንዲደርስ ያበቁት አሠልጣኝ ባለፈው ሰሞን ከሥራ እንዲሰናበቱ ከተደረገ ወዲህ ፣ የአገሪቱ የእግር ኳስ ይዞታ ፣ አሁንም በእግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ ማነጋገሩን እንደቀጠለ ነው። ዶቸ ቨለም፣ በኅብረትም ሆነ በቡድን የሚካሄደውን ፤ ኢትዮጵያም ውስጥ እጅግ ተወዳጅ የሆነውን እግር ኳስ ፣ በሀገሪቱ ከሚገኝበት ደረጃ የላቀ እመርታ እንዲያሳይ ፤ በይበልጥ እንዲሻሻል ምን ይበጃል በማለት 3 እንግዶችን ለውይይት ጋብዟል።
ሙሉ ዉይይቱ የድምፅ ማድጫዉን ምልክት በመጫን ይከታተሉ።

ተክሌ የኋላ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ