የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባዔ
ሰኞ፣ ጥቅምት 22 2003ማስታወቂያ
ከአዲስ አባባ፤ ታደሰ እንግዳው በላከልን ዘገባ ላይ እንደገለጠው፣ የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ውን ጉባዔ ሲያጠናቅቅ፣ ባወጣው መግለጫ ፣ በቤተ-ክርስቲያኒቱ በንሠራፋው ምዝበራና ሙስና ሳቢያ፣ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መገነቱ በሂሳብ መርማሪ በኩል መረጋገጡ ታውቋል። ባለፉት 3 ዓመታት በቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ሙስናዊ አሠራር ተንሠራፍቷል፣ በአባ ፓውሎስ ዙሪያ በተሰባሰቡ ግለሰቦች አማካኝነት ከሲኖዶስ እውቅና ውጪ፣ አምባገነናዊ አሠራር ታይቷል በማለት የተቹት የሲኖዶስ አባላት፣ በቦሌ ደብረ-ሳሌም መድኃኔ-ዓለም የቆመው የአባ ፓውሎስ ሀውልትም ሆነ በየአድባራቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተሠቀሉ ፎቶግራፎች ተነስተው በመዘክር እንዲቀመጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
ታደሰ እንግዳዉ
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሐመድ