1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን

ዓርብ፣ ኅዳር 3 2008

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ዓለም ዋንጫው ውድድር ለማለፍ አንድ ውድድር ሲቀረው፤ ባለፈው ሳምንት በጋና ብሔራዊ ቡድን ተሸንፎ ከዓለም ዋንጫው ውድድር ተገልሏል።

https://p.dw.com/p/1H5Hd
Symbolbild Fußball Tor Netz
ምስል Fotolia/somkanokwan

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን

ይሁንና ይህ ብሔራዊ ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመሰረተ እና የሚተጉ ተጫዋቾች እንዳሉት ይነገራል። ብዙዎች እስካሁን ድረስ ስለ እግር ኳስ ጨዋታ ሲነሳ የወንድ ጨዋታ ብቻ አድርገው ነው የሚመለከቱት። እኢአ በ2011 ዓም የሴቶች የእግር ኳስ ዋንጫን ባስተናገደችው ጀርመን በተደረገ አንድ የህዝብ መጠይቅ መሠረት የጀርመን ምርጥ የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋች ስለሚባሉት ብርጊት ፕሪንስ እና ናዲን አንግረር ከተጠየቁት መካከል ሰምተው የሚያውቁ ግማሽ ያህሉ ብቻ ነበሩ። ይሁንና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሴቶች እግር ኳስ ጨዋታ እንደ ወንዶቹም ባይሆን ተወዳጅ እየሆነ መጥቷል። ወደ ኢትዮጵያ ያመራን እንደሆነ ደግሞ ሰሞኑን የብዙዎችን ልብ ስቦ የነበረው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ያደረጋቸው ግጥሚያዎች ናቸው።
ወጣት ሎዛ አበራ የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አምበል እንዲሁም የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች ናት። የኳስ ፍቅር ያደረባት በልጅነቷ ነው።በዚሁ ቡድን ውስጥ ምክትል አምበል የሆነችው እና የዳሸን ቢራ ክለብ ተጫዋች ሄለን እሸቱም መጀመሪያ ላይ ኳስ መጫወት የጀመረችው በመጀመሪያ እና ሰፈር ውስጥ ነው።
የ 19 ዓመቷ ሎዛ በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ናት። ከእግር ኳስ ልምምድ እና ግጥሚያ ጋር ጊዜው ቢጠብባትም ሁለቱን ጎን ለጎን ማስክሄድ እንደቻለች ትናገራለች። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾቹ « አብረን መሰልጠን የጀመርነው አምና ክረምት ሐምሌ ወር ላይ ነው » የምትለው የቡድኑ አምበል ሎዛ፤ በቡድኑ ውስጥ ያለውም ግንኙነት እጅግ በጣም ጥሩ እንደሆነ ነው የተናገረችው
የዚህ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አስራት አባተ ደግሞ ስለቡድኑ አመሰራረት እና ስኬት የገለፁልን አለ። ሁሉንም በድምፅ ያገኙታል።

Fußball Tor Netz
ምስል Fotolia/sharpshutter22


ልደት አበበ
አርያም ተክሌ