1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ካርዲናል በዓለ ሢመት

ሰኞ፣ የካቲት 16 2007

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አባ ብርሃነ የሱስ ፤ ከሁለት ወራት ገደማ በፊት ከሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቀነ ጳጳሳት ፍራንስስ ፣ የካርዲናልነት ማዕረግ ማግኘታቸው የሚታወስ ነው።

https://p.dw.com/p/1EgGW
ምስል DW/G. Tedla HG

ያኔ ፣ በዓለም ዙሪያ ፣ የካርዲናልነት ማዕረግ ካገኙት 15 ካቶሊካውያን ሊቃነ-ጳጳሳት አንዱ ካርዲናል ብርሃነ የሱስ፤ አዲስ አበባ ውስጥ፤ በካቶሊካዊቷ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ፤ በአፍሪቃ ከሚገኙ ጳጳሳትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በሥርዓተ ቅዳሴ ሢመታቸው ተከብሮአል ። በኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ታሪክ ፤ ከቫቲካን በካርዲናል ደረጃ ሹመት ለማግኘት አባ ብርሃነ -የሱስ ሁለተኛ ናቸው ።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ