የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካ-ከዶክተር ነጋሶ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ሰኞ፣ ኅዳር 28 200207 12 09
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳና የቀድሞዉ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ስዬ አብረሐ ለምሥረታዊ አበክረዉ የጣሩለት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዲሞክራሲያዊ መድረክ ወደ ጥምረት-ሲያመራ፥ ሁለቱ ፖለቲከኞች የአንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ተቀይጠዋል።ሰሞኑን።ዶክተር ነጋሶን ዛሬ-ለምን እና እንዴት ብለናቸዋል።ከመድረክ ምሥረታ ሒደት ይጀምራሉ።እንስማቸዉ።
ድምፅ
የምርጫዉ ሒደት በምርጫ ሥነ-ምግባር ደንብ ድርድር ነዉ-የተጀመረዉ። የምርጫዉ ሥነ-ምግባር ይዘት በተለይም የድርድሩ ሒደት ትልቁን ተቃዋሚ የፖለቲካ ማሕበራት ስብስ- መድረክን ቅር ቢያሰኝም-ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ እና ሰወስት ተቃዋሚዎቹ የተስማሙበትን ሐሳብ-ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች መቀበላቸዉ ተሰምቷል።ዶክተር ነጋሶ ግን ደንቡን-ለዲሞክራሲ አደገኛ ይሉታል።
ድምፅ
ግን ለምን።
ድምፅ
ያም ሆኖ ደንቡ ሕግ እንዲሆን ለተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።
ድምፅ
ዶክተር ነጋሶ-አደገኛ ያሉት አዋጅ-ሕግ ከሆነ የተቃዋሚዎች በተለይም የመድረክ ሚና-ምንነት በርግጥ ያነጋግራል።መልስ አላቸዉ።ዶክተር ነጋሶ-ከፕሬዝዳትነት ሥልጣናቸዉ ሲሰናበቱ-በፕሬዝዳትነት ያገለገለ-ፖለቲከኛ የፖለቲካ ፓርቲ አባል እንዳይሆን በሕግ-ተደንግጓል።ሕጉ አልተሻረም።እሳቸዉ ግን-የአንድነት ፓርቲን ተቀላቅለዋል።
ድምፅ
ይላሉ።ሌላም-ምክንያት አላቸዉ።ከሌሎቹ የፖለቲካ ማሕበራትን አንድነትን-ከመረጡበት ብዙ ምክንያቶች የፓርቲዉ መሪ ጥንካሬና ሴትነት- አንዱ ነዉ።በወይዘሪት ብርቱካን-ምክንያት።
ድምፅ
እነዚሕንና ሌሎችንም-አንስተናል።ሳምንት ጠብቁን።ነጋሽ መሐመድ ነኝ እስከዚያዉ ቸር ያሰማን።
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ