1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የረሀብ ስጋት እና መንስዔው

ረቡዕ፣ ጥቅምት 18 2002

በኢትዮጵያ በድርቅ ምክንያት ከስድስት ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልገዋል።

https://p.dw.com/p/KHcw
ምስል AP

በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ወራት አስፈላጊው ርዳታ ካልቀረበ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገው ሰው ቁጥር ወደ አስራ አራት ሚልዮን ከፍ ሊልና ከሀያ አምስት ዓመታት በፊት በሀገሪቱ ከደረሰው የብ ሰው ህይወትን ካጠፋው የከፋሁኔታ እንደሚፈጠር የተመ የህጻናት መርጃ ድርጅት፡ ዩኒሴፍ፡ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችና የብሪታንያ የውጭ ልማት ሚንስትር ዳግላስ አሌክሳንደር አስጠንቅቀዋል። የዚሁ ተደጋጋሚ የረሀብ ስጋት መንስዔ ምን ሊሆን ይችላል? የለንደን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህ ፕሬፌሰር ማሞ ሙጬን በደቡብ አፍሪቃ እና ዶክተር ሰይድ ሀሰንን ከአሜሪካ በስልክ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ድልነሳ ጌታነህ/አርያም ተክሌ