1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ

ረቡዕ፣ መስከረም 19 2008

በዚሁ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተነስተዋል። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በምክር ቤቱ አባልነት ለመመረጥ ያቀረበችው ጥያቄ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ ቀርቦበታል።

https://p.dw.com/p/1GgB1
Schweiz 30. Sitzung des UN-Menschenrechtsrates
ምስል picture-alliance/dpa/S. Di Nolfi

[No title]


30ኛው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባኤ ጄኔቭ ስዊትዘርላንድ ውስጥ እየተካሄደ ነው። ከዚሁ ጉባኤ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ይዞታ ላይ ያተኮረ ስብሰባ ከትናንት በስተያ ተካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት ይዞታ የሚከታተሉ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ዓለም ዓቀፍ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም የመንግሥት ተወካዮች ተገኝተው ነበር። በዚሁ ስብሰባ ላይ በኢትዮጵያ ይፈፀማሉ የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተነስተዋል። ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በምክር ቤቱ አባልነት ለመመረጥ ያቀረበችው ጥያቄ በስብሰባው ላይ ተቃውሞ ቀርቦበታል።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ