1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ ጉዳዮችና ዩኤስ አሜሪካ 

ማክሰኞ፣ የካቲት 14 2009

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ተጠያቂ የሚያደርግ ረቂቅ ዉሳኔ በዩናይትድ ስቴትስ ተወካዮች ምክር ቤት እንደገና ቀረበ። የረቂቅ ዉሳኔዉ ሃሳብ በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ሕዝብ ላይ በደል ያደረሱ ባለሥልጣናት ሥልጣን ላይ እያሉና ስልጣን ሲለቁም የሚጠየቁበት ነዉ ተብሎአል።

https://p.dw.com/p/2XzKP
USA Weißes Haus in Washington
ምስል picture alliance/dpa/M. Reynolds

Ber. WDC. (Äthiopien Menschenrecht und U.S.A.) - MP3-Stereo


ረቂቅ ሕጉ ከፀደቀ ባለስልጣናቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠያቂ እንዲሆኑ እና በዉጭ ያስቀመጡት ንብረት እንዲያዝ ሁሉ ያስገድዳል። በዩኤስ አሜሪካ ምክር ቤት የዉጭ ጉዳዮች የአፍሪቃ ንዑስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ክሪስ ስሚዝ ለዶይቼ ቬለ እንደገለፁት እኛ የኢትዮጵያ ሕዝብን እናከብራለን ሕዝቡን የሚከብር መንግሥትም እንዲኖርም እንፈልጋለን ሲሉ መናገራቸዉን የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል።


መክብብ ሸዋ 
አዜብ ታደሰ