1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የተቃዉሞ ፓርቲዎች ወቅታዊ ይዞታ

እሑድ፣ ሐምሌ 13 2006

ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ጥርጊያ የሚከፍተዉ በነፃ የመደራጀት መብት በሕገ መንግስት ተደንግጎ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ከሁለት አስርት ዓመታት ያላነሰ ጊዜ አስቆጥሯል። በዚህ ጊዜም በሥልጣን ላይ ያለዉን ማለትም ገዢዉን ፓርቲ ለመፎካከር በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተቋቋሙ ፈርሰዋል።

https://p.dw.com/p/1CfLm
Karte Äthiopien englisch

ተጠናክረዉ የቀጠሉም ቁጥራቸዉ በጣት ተቆጥሮ የሚወሰን አይደለም። የፓርቲዎቹ ዳራና መርሕ እንደየተነሱለት ዓላማ ብሔራዊና ጎሳዊ ሊሆን ብችልም ድምፃቸዉ ግን ተመሳሳይ ነዉ። ሁሉም ለዉጥን ያዜማሉ፤ እነሱ የሚያልሙት ለዉጥ እንዲኖርም የየራሳቸዉን ስልት ይከተላሉ ወይም እንከተላለን ይላሉ። በተለይ ከ1997 ወዲህ ስለሥርዓት ለዉጥ ደጋግመዉ ሲናገሩ ቢደመጥም ተባበሩ ሲባል ሲበታተኑ፤ ጠነከሩ ሲባል ሲዳከሙ መታየቱ ጉዟቸዉ ገና ሩቅ መሆኑን በግልፅ ማመላከቱን ብዙዎች ይስማማሉ። እነሱ ለመበተን፣ መዳከማቸዉ ፈርጣማ ክንዱን በየአቅጣጫዉ የሚያሳያቸዉ ገዢዉን ፓርቲ ተጠያቂ ያደርጋሉ። ገዢዉ ፓርቲ ማለትም መንግስት ደግሞ የራሱን ትችት አልፎ ተርፎም ዉግዘት ይሰነዝራል። ቁጣዉ ሲንርም እስር ቤት የሚወረዉራቸዉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከዕለት ወደዕለት ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ። ሙሉዉን ዉይይት ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ!

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ