1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት

እሑድ፣ መስከረም 9 2008

አንዳንድ የኤኮኖሚ ባለሞያዎች ችግሩ የሀገሪቱ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ነው ያለው ይላሉ። መንግሥት ችግሩን የሚያባብሱት ስግብግብ የሚላቸው ነጋዴዎች ናቸው ሲል ይከሳል።

https://p.dw.com/p/1GYvq
"Mercato-Markt" in Addis Abeba, Äthiopien
ምስል picture alliance/kpa

[No title]

ካለፈው ዓመት አጋማሽ አንስቶ በኢትዮጵያ የሸቀጦች በተለይም የምግብ ነክ ምርቶች ዋጋ በፍጥነት እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል። ባለፉት ሦስት ወራት ደግሞ የተወሰኑ ምግብ ነክ ሸቀጦች እስከዛሬ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ዋጋቸው ንሯል። ለዋጋ ጭማሪው በምክንያትነት ከሚነሱት ውስጥ የአቅርቦትና ፍላጎት አለመመጣጠን አንዱ ነው። አንዳንድ የኤኮኖሚ ባለሞያዎች ደግሞ ችግሩ የሃገሪቱ የኤኮኖሚ ፖሊሲ ላይ ነው ያለው ይላሉ። መንግሥት ችግሩን የሚያባብሱት ስግብግብ የሚላቸው ነጋዴዎች ናቸው ሲል ይከሳል።

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ