1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ

ሐሙስ፣ መስከረም 6 2003

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መንግስታቸው በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የአስራ አምስት በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ማቀዱን አስታውቀዋል ። በዚህ ጊዜ ውስጥም አገሪቱ ያለ ውጭ ዕርዳታ ህዝቧን ለመመገብ ዕቅድ ማውጣቷንም አቶ መለስ ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/PDsP
ምስል picture alliance/dpa

ይሁንና ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት አስመዘግባለሁ ያለችው ይህ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊሳካ መቻሉ የአፍሪቃ ቀንድ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ ክርስቶፈር ኢድስ ለዶይቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት አጠራጣሪ ነው ። በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናንን ለማረጋገጥም እንደተንታኙ አንዳንድ መርሆች ማስተካከል ይገባቸዋል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ