የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ስምምነት
ማክሰኞ፣ የካቲት 15 2008ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በሦስትዮሽ ሁለገብ የልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት በቅርቡ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ሦስቱ ሃገራት እዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ና የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ዑመር አልበሽር ግብፅ ሻርም ኤልሼክ ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ የጋራ ትብብራቸውን በሚያጠናክሩበት መንገድ ላይ ከተወያዩ በኋላ ነው ። መሪዎቹ በትብብር ለመስራት የተወያዩት እዚያው ሻርም ኤል ሼክ በመካሄድ ላይ ከነበረው የአፍሪቃ መዋዕለ ንዋይ ፍሰት መድረክ ጎን ለጎን ባካሄዱት ስብሰባ ነበር ። ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በተለይ የግብፅ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ቀጣና የመገንባት እቅድ ይዘዋል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ