1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነት እና CPJ

ዓርብ፣ ጥቅምት 18 2009

CPJ በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በተለያዩ ሐገራት ያለዉን የጋዜጠኝነት ነፃነትን ባጠናበት ዘገባዉ እንዳለዉ ኢትዮጵያ መገኛኛ ዘዴዎችን በመዝጋትና ጋዜጠኞችን በማሰር የመጀመሪያዉን ደረጃ ከያዙት ሐገራት ተርታ ተሰልፋለች

https://p.dw.com/p/2Rqdn
Logo CPJ
ምስል APTN

(Beri.WDC) Äth.Pressefreiheit-CPJ - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ በደነገገዉ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አማካይነት ወትሮም ያመነመነመዉን የፕሬስ ነፃነትን ይበልጥ እየደፈለቀዉ መሆኑን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እስታወቀ።CPJ በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት በተለያዩ ሐገራት ያለዉን የጋዜጠኝነት ነፃነትን ባጠናበት ዘገባዉ እንዳለዉ ኢትዮጵያ መገኛኛ ዘዴዎችን በመዝጋትና ጋዜጠኞችን በማሰር የመጀመሪያዉን ደረጃ ከያዙት ሐገራት ተርታ ተሰልፋለች።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ