1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በጀርመን ያደረጉት ውይይት

ዓርብ፣ ኅዳር 10 1997

ኢትዮጵያና ጀርመን ይፋ ዲፕሎማቲክ ግንኙነት የጀመሩበት አንድ መቶኛ ዓመት የፊታችን መጋቢት የሚከበርበትን ድርጊት አስመልክቶ ሁለቱ ሀገሮች በጀመሩት ዝግጅት መደዳ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ባለፈው ኅዳር አንድና ሁለት በበርሊን ይፋ ጉብኝት ማድእረጋቸው ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/E0kk

ሁለቱ ሀገሮች በዚሁ ፀንቶ በቆየው ግንኙነታቸው መልካሙን ጉድኝት የፈጠሩ ሲሆን፡ በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ጉድኝቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ጠቅላይ ሚንስትሩ አመልክተዋል። በበርሊኑ ቆይታቸው ከጀርመናውያኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፡ በጀርመን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ከጀርመናውያን ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል። በዶቸ ቬለ አዘጋጅነት ከጀርመናውያን ጋዜጠኞች ጋር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባደረጉት ሰፋ ያለ ውይይት ከተነሱት በበርካታ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች መካከል ቀጥሎ የጥቂቶቹን ይዘት አቅርበናል።