1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ያንጋፋና የወጣት ፖለቲከኞችዋ አንድነትና ልዩነት

ነጋሽ መሐመድ
እሑድ፣ መጋቢት 3 2009

ብዙ ወጣቶች ትምሕርት፤ ደሞዝ፤ ትዳር፤ ፍቅር፤ ከሁሉም በላይ ሕይወታቸዉን የሰዉለት ትግል ለዛሬ እና ለመጪዉ ትዉልድ ያስገኘዉ ዉጤት በጎ መጥፎነት በርግጥ እንደየተመልካቹ የሚለያይ አንዳዴም የሚቃረን ነዉ።ከአርባ እና ከሐምሳ ዓመታት በኋላ አሁንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የዴሞክራሲ፤ የፍትሕ፤ የምጣኔ ሐብት ጥያቄ መልስ አላገኘም የሚሉ ብዙ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/2Yz17
Karte Äthiopien englisch

NM - MP3-Stereo

በተደጋጋሚ እንደተባለዉ የ1960ዎቹ ኢትዮጵያዊ ወጣት የሐገሪቱን መሠረታዊ ፖለቲካዊ፤ ፍትሐዊና ምጣኔ ሐብታዊ ችግሮችን ለማስወገድ ከአደባባይ አመፅ እስከ ሕቡዕ ተቃዉሞ፤ ከፁሁፍ ክርክር እስከ ነፍጥ ፍልሚያ ታግሏል።ከነባሩ ፊዉዳላዊ ሥርዓት ተጠቃሚዎች ጋርም፤ እርስበርስም ተዋግቷን።የደም፤ አካል፤የሕወት መስዋዕትነት ከፍሏል።
ብዙ ወጣቶች ትምሕርት፤ ደሞዝ፤ ትዳር፤ ፍቅር፤ ከሁሉም በላይ ሕይወታቸዉን የሰዉለት ትግል ለዛሬ እና ለመጪዉ ትዉልድ ያስገኘዉ ዉጤት በጎ መጥፎነት በርግጥ እንደየተመልካቹ የሚለያይ አንዳዴም የሚቃረን ነዉ።ከብዙ መስዋዕትነት በኋላ፤ ከአርባ እና ከሐምሳ ዓመታት በኋላ አሁንም የኢትዮጵያ ሕዝብ የዴሞክራሲ፤ የፍትሕ፤ የምጣኔ ሐብት ጥያቄ መልስ አላገኘም የሚሉ ብዙ ናቸዉ።ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚታዩ ዉስብስብ ችግሮች በ1960ዎቹ ለትግል የተነሳሳዉን ወጣት የሚወቅሱም አሉ።ለምን? የኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ የአንጋፋና የወጣት ፖለቲከኞችዋ አንድነትና ልዩነት በዛሬዉ ዉይይታችን ባጭሩ የምናነሳዉ ጥያቄ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ልደት አበበ