1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮችና የወይዘሪት ብርቱካን ሚድቅሳ አስተያየት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 16 2001

ድረቅ-ረሐብ መታወቂያዋ፥ የርስ በርስ ጦርነት መለያዋ እንደሆነ አመታት ያስቆጠረችዉ ኢትዮጵያ ከቅርብ አመታት ወዲሕ በፖለከኞችዋ ዉዝግብ

https://p.dw.com/p/G1C6
ኢትዮጵያምስል AP GraphicsBank/DW

የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲን ያሁን እንዴትነት የጠየቅሁት የአዲስ አበባ ነዋሪ-በሁለት ጣቶቹ የእንግሊዝኛዉ V ፊደል አሳየኝ-እየሳቀ።የድርጅቱ መለያ ነበር።«ቅድሞ እንደዚያ ነበር» አለኝ።ቀጠለ፥- አሁን ግን የሁለቱን እጆቹን አስር ጣቶች በሙሉ ቀሰራቸዉ፥-ቅንጅቶች አሁን አስር ናቸዉ እንደማለት።አስርም ሆነ። እሁለት ከተከፋፈሉት የቅንጅት መሪዎች አንድነት ለፍትሕና ለዲሞክራሲ ፓርቲን በቅርቡ የመሠረቱትና የሚመሩት ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ አዉሮጳን እየጎበኙ ነዉ።ወይዘሪት ብርቱካን እስከ ትናንት ብሪታንያ፥ ቤልጂግ፥ሲዊድን፥ ሆላንድ፥ እና እዚሕ ጀርመን ባደረሰ ጉብኝታቸዉ በየሐገሩ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉን አንድ ጥያቄ በተደጋጋሚ ይነሳ ነበር-ይላሉ።እንስማቸዉ።