1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጽያ የወራት ስያሜና ፍችዉ

ሐሙስ፣ ኅዳር 2 2003

እህልን በጥቅምት ልጅን በጡት፣ በጥቅምት አንድ አጥንት ሳንላችሁ፣ ዛሪ ህዳር ሁለት አልን! ጥቅምትን ካነሳን ዘንዳ፣ ማር እና እህል በጥቅምት ይቆጠባል ይባላል!

https://p.dw.com/p/Q5d1
ምስል Helge Bendl

የጥቅምት ማር በመድህኒትነቱ ታዋቂ በመሆኑ፣ በጥቅምት ጎተራዉም ስለሚጎድል መቆጠብ እንዳለበት ለመግለጽ። ስለጥቅምት ብዙ ይባላል፣ ዛሪ ህዳር ከባተ በሁለተኛ ቀኑ ደግሞ በህዳር እሸት ሁሉ ዳር ዳር ብለናል! የአስራ ሶስት ወር ጸጋ ኢትዮጽያችን ከርዕሰ አዉደ አመት ከመስከረም ጀምሮ እስከ አስራ ሶስተኛ ወር ጳግሜ ድረስ ወራቱ የተለያዩ መጠሪያዎች አባባሎች ስነ-ቃሎች እናገኛለን! የሚገርመዉ ደግሞ የኢትዮጽያ የወራት ስያሜ ከግብርና ህይወት ከእርሻ ጋር የተያያዘ መሆኑ ነዉ። በለቱ ዝግጅታችን ስለ ኢትዮጽያ የወራት ስያሜ እና ከወራቶች ጋር ስለሚባሉ ስነ-ቃሎች እና ወቅቶች ባለሞያ ጠይቀን ልናካፍል ይዘናል ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ