1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጽያ ፖለቲከኞች ዉይይት እና ዉዝግብ

ዓርብ፣ ጥቅምት 27 2002

በቅርቡ በኢትዮጽያ የምርጫ ህግ ላይ የተስማሙት የገዥዉ የኢሃዲግ ፓርቲ እና አራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ማህበራት በስምምነቱ ዝርዝር ጉዳይ ላይ ይነጋገራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነበር።

https://p.dw.com/p/KQ55
ምስል picture alliance/dpa

እስካሁን ግን አራቱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ዉይይት ስለመጀመር አለመጀመራቸዉ በግልጽ የታወቁ ነገር የለም የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ስብሰባዉ ስለሚኖረዉ ይዘት ከተሳታፊዎቻቸዉ መካከል የተወሰኑትን አነጋግሮ ነበር። በተያያዘ ዜና በዉይይቱ ላይ የማይሳተፈዉ የኢትዮጽያ ፊደራላዊ ዲሞክራሲያዊ መድረክ አራቱን ፓርቲዎች እና የምርጫ ቦርዱን ወቅሶአል። መድረክ እና የምርጫዉን ህግ የፈረሙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከሚያወዛግቡት ጉዳዮች አንዱ የፖለቲከኛ እስረኞች በተለይም የፍትህ አንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መሪ ወይዘሪት ቡርቱካን ሚደቅሳ ከእስር መፈታት ነዉ።

ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ፣ ነጋሽ መሃመድ