1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ሱዳን ድንበር መካለል

ሐሙስ፣ መስከረም 21 2002

በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ከመጪዉ መስከረም 29ቀን 2002ዓ,ም ጀምሮ የድንበር ማካለል ተግባር እንደሚከናወን እየተነገረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/JvmC
ምስል AP GraphicsBank/DW

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለዉ የኢትዮ ሱዳን ድንበር ኮሚቴ እንደሚለዉ በዚህ ሂደት የሱዳን መንግስት ከሁመራ እስከ ጎሙጎፋ ጫፍ ድረስ ወደ1,600 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለዉን መሬት ያገኛል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን ያነጋገረዉ በአሜሪካን የሱዳን ኤምባሲ ዝርዝር መረጃ እንደሌለዉ ሲገልፅ፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደግሞ ወደዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የህግ ክፍል መርቶታል። ከመንግስት ወገን ግን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።

አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ