1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንተርኔት አገልግሎት እገዳ በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 4 2010

የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ፕሮጄክት የተባለዉ ተቋም ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አገልግሎቱን ከማስፋፋት ይልቅ ለመገደብ እና ተጠቃሚዎችን ለመሰለል የሚያወጣዉ ገንዘብም ብዙ ነዉ

https://p.dw.com/p/2pKPK
Symbolbild Virtual Private Network VPN

(Beri.WDC) Syber security in Ethiopia - MP3-Stereo

አንጡራ ወይም የእንግሊዝኛ ሥሙ ኢንተርኔት ነዉ።አንዳዶች አምደ-መረብ ይሉታል።ሌሎች በይነ-መረብ።ብዙዎች ያዉ እንደ ገና ስሙ ኢንተርኔት።ኢንተርኔትም አልነዉ ሌላ አገልግሎቱ ያዉ ነዉ።ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ኢትዮጵያ ዉስጥ ይሕን አገልግሎት የሚጠቀመዉ ከሐገሪቱ ሕዝብ አስራ-አምስት ከመቶ ቢሆን ነዉ።ይሕ አልበቃ ብሎ፤  ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ነፃነትን በከፍተኛ ደረጃ ከሚደፈልቁ  ሐገራት አንዷ መሆንዋን በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት አጋልጧል።የኢትዮጵያ የሠብአዊ መብት ፕሮጄክት የተባለዉ ተቋም ከዩናይትድ ስቴትስ እንዳስታወቀዉ የኢትዮጵያ መንግሥት አገልግሎቱን ከማስፋፋት ይልቅ ለመገደብ እና ተጠቃሚዎችን ለመሰለል የሚያወጣዉ ገንዘብም ብዙ ነዉ።የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ