1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንተርኔት ዓለም-አቀፍ የመረጃ ድር፣ 20ኛ ዓመት፤

ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2001

ዓለምን በኮምፒዩተር መረጃ ድር ያስተሣሠረው፣ World Wide Web(W W W) በእንግሊዝኛው የፊዚክስ ምሁር Tim Berners-Lee የቀረበ በረከት ነው።

https://p.dw.com/p/HF2K
የኢንተርኔት ፣ ዓለም -አቀፍ የመረጃ ድር(WWW) ፈልሳፊ፣ እንግሊዛዊው የፊዚክስ ምሁር፣ቲም በርነርስ-ሊ፣ በ 20ኛው ዓመት ክብረ-በዓል፣ ጀኔቭ አቅራቢያ በ CERN የምርምር ጣቢያ በሚገኘው መሥሪያ ቤታቸው፣ምስል picture-alliance/ dpa

እኒህ ሰው፣ እስዊትስዘርላንድና ፈረንሳይ ድንበር ላይ በሚገኘው የአቶም ምርምር ጣቢያ(CERN)ውስጥ ከሌሎች 3 ባልደረቦቻቸው ፣ Robert Cailliau, Ben Segal እና Jean-Francois Groff ጋር ሆነው እዚህ ደረጃ ያበቁት የኮምፒዩተር የመረጃ መረብን ሆነ ድር የተፈለሰፈው እ ጎ አ በመጋቢት ወር 1989 ዓ ም ሲሆን፣ ለህዝብ አግልግሎት መስጠት የጀመረው፣ እ ጎ አ ከ 1993 ዓ ም ወዲህ ነው።

በኦክስፎርድ ፊዚክስ ካጠኑ በኋላ፣ በ CERN ለመመራመር ወደ ጀኒቭ ያመሩት ቲም በርነርስ ሊ፣ ከ 20 ዓመት በፊት የ «ሶፍት ዌር ኢንጅኒየር » በነበሩበት ጊዜ፣ ለአለቃቸው ማይክል ሴንዶል፣ መረጃእንዴት ሊቀርብና ሊያዝም እንደሚችል ሐሳብ አቅርበው ፣ አለቃቸው እንደዋዛ ይቀበሉላቸዋል።

ዓለም አቀፍ የመረጃ ግንኙነትን እንዲሠምር ሊያደርግ የሚችለው፣ በጽሑፍ የቀረበው ሐሳብ፣ ውስብስብ ያለና ፣ ክብ የተደረገበት ስዕል ነበረበት። ማዕከሉ ላይም Mesh የሚል ስም የተጻፈበት ነበረ። ሆኖም በርነርስ-ሊ፣ “Mesh” ፣ “Mess“ (ዝብርቅርቅ) የሚል ዓይነት ድምፅ ስላለው፣ ስሙን መለወጥ ፈለጉና፣ እ ጎ አ በ 1990 ዓ ም፣ World Wide Web የተሰኘውን ስያሜ ሰጡት።

AFP/Wikipedia

ተክሌ የኋላ፣

ሸዋዬ ለገሠ፣