1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርት

Merga Yonas Bula
ማክሰኞ፣ ግንቦት 29 2009

ወደ መሰናዶ ትምህርት የሚያስገባዉ የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ባለፈዉ ሳምንት ከሰኞ እስከ ረቡዕ ድረስ ባሉት ቀናት ተጠናቋል።

https://p.dw.com/p/2eCgh
Äthiopien Addis Abeba Universität Kommunikation Internetsperre
ምስል DW/J. Jeffrey

M M T/ The Impact of Internet Disruption in Ethiopia - MP3-Stereo

የ12ኛ ክፍል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ደግሞ ከትላንት ጀምሮ እየተሰጠ ነዉ። በፈተናዉ ወቅት የኢንቴርኔት አገልግሎት ተቋርጧል። ዶቼ ቬሌ ባለፈዉ ሳምንት ያነጋገራቸዉ በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አጀንሲ የህዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ ጉዳዩን አስመልክቶ አጅንሲዉ ጉዳዩን እንደማያዉቀዉ ተናግሮ ነበር።

ይሁን እንጅ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ትላንት በሰጡት መግለጫ የኢንተርኔት አግልግሎት የተቋረጠበትን ምክንያት ይፋ አድርጎታል። ባለስልጣኑ  «ለፈተና የሚቀመጡ ተማሪዎችን ስነ ልቦና ለመጠበቅና ፈተናውን ተረጋግተው እንዲፈተኑ ለማድረግ የተወሰደ እርምጃ» መሆኑን ነዉ የገለጹት።

በመንግሥት የተወሰደዉ የኢንተርኔት አገልግሎትን የማቋረጥ ርምጃ ያስከተለዉን ተፅዕኖ በተመለከተ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ ያልፈለጉ በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ የአዲስ አበባ ነዋሪ መንግሥት የሰጠዉን ምክንያት ቢቀበሉም መቋረጡ ግን መረጃ ለማገኘት ግእንቅፋት እንደሆነባቸዉ ይናገራሉ።

ጀሳን ሞስል ከ20 ዓመት በፊት በወሎ ዞን በወረኢሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት በመምህርነት ለሁለት ዓመት አገልግለዋል። አሁን ደግሞ ለንዳን በሚገኘዉ በቻታም ሃዉስ በአፍሪቃ ፕሮግራም ተባባሪ ተመራማር በመሆን የኢትዮጵያን የማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይተነትናሉ።

«መንግሥት የትምህርት አግልግሎት ለማኅበረሰቡ የማድረስና ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸዉን ስረዓት የማስተዳደር ትልቅ ሚና አለዉ። ስለዚህ ነዉ እንደ ባለፈዉ ዓመት ፈተና ሾልኮ እንዳይወጣ በጣም በጣም ብዙ ወጭ የሚያስወጣዉን ኢንቴርኔት የመዝጋት ርምጃ የወሰደዉ። ይህም የሚያመለክተዉ የፈተናዉን ደህነት ለመጠበቅ ያላቸዉን ስልት ነዉ። ከዚህም ሌላ መንግሥት የማኅበራዊ መገናኛዉን አገልግሎት ለመቆጣጠር የሚያስችለዉ ሌላ መንገድም ለማሳካት ፍላጎት አለዉ የሚለዉን ጥያቄም አብሮ የሚያስነሳ ነዉ።»

288, 634 ተማሪዎች ሐሙስ የሚጠናቀቀዉን የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደሚፈተኑ ዘገባዎች ያሳያሉ። የኢንተርኔት አገልግሎቱ መቋረጥም እስከዚያዉ ይዘልቃ ተብሎ ይገመታል።

መርጋ ዮናስ

ሸዋዬ ለገሰ