1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንዱስትሪ ዐውደ ርእይና «ሮቦቶች»

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 7 2007

የታሕታይ ሳክሰኒ (ኒደርዛኽሰን) ፌደራል ክፍለ ሀገር ርእሰ ከተማ ፣ ሐኖፈር ፤ ለዐውደ ርእይ በሚቀርቡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ረገድ ገናና ስም ያላት ከተማ ናት። በያመቱ በሚያዝያ ወር ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሩሪ ትርዒት የምታዘጋጅ

https://p.dw.com/p/1F91m
ምስል Deutsche Messe AG/R. Jensen

ስትሆን፤ በየጊዜው «የወደፊቱ ፋብሪካ» በሚል ርእሰ ጉዳይ ውይይት ፤ ምክክር የተጓደለበት ጊዜ የለም። «የሮቦቶትና የሰው ቡድን» በተሰኘው መፈክር ባለፈው ሰኞ በተከፈተው ዐውደ ርእይ፣ ከ 70 ሃገራት የተውጣጡ 6,500 የኢንዱስትሪው ዐውደ ርእይ ተሳታፊዎች ለመካፈል በቅተዋል።

3 ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ --መጀመሪያ ፣ ቻይና ከሰሞኑ ደግሞ ፣ ሕንድ ፤ የሐኖቨር ዐውደ ርእይ ዋና ደንበኞች ለመሆን በቅተዋል። ቻይና በ«ዲጂታል እንዱስትሪ--ሕንድ በሮቦትና አጠቃላይ ኢንዱስትሪ!

ቻይናና ሕንድ ፤ ሁለቱም ከአዳጊ ሀገራት በይበልጥ ላቅ ባለ የዕድገት እመርታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው እሙን ነው። በሕዝብ ብዛትም በዓለም ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ እንደያዙ የሚገኙ እነዚሁ ሃገራት ናቸው!

Hannover Messe Highlights 2015
ምስል AFP/Getty Images/T. Schwarz

እ ጎ አ ፣ በ 1947 ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነጻነቷን ያገኘችው ሕንድ፣ የመጀመሪያ ጠ/ሚንስትር ጃዋኻራል ኔህሩ ባደረጉት አበረታች ተግባር ፣ ሳይውል ሳያድር ነበር የሥነ ቴክኒክ ተቋም የመሠረተች። ከዚያም በመነሣት፤ ሥነ-ሕይወትን ያጣመረው የግብርና ምርምር ቀጠለ።የሥነ -ፈለክ ምርምሩም ፤ በያኔዋ ሶቭየት ሕብረት ድጋፍ ደርጅቶ፣ ዛሬ ከታወቁት ሕዋ አሳሽ መንግሥታት መካከል አንዷ ለመሆን አብቅቷታል። ጨረቃ አሳሽ «ቻንድራያን 1 »የተባለች መንኮራኩር ፣ ቀጥሎም ከ 2 ዓመት በፊት በኅዳር «ማንጋሊያን » የተሰኘ ስለማርስ ጥናት የሚያደርግ መንኮራኩር በተሣካ ሁኔታ ማምጠቋ የሚታወስ ነው። ለሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የቻይናን ያክል በቂ ገንዘብ አልመደበችም የምትባለው ሕንድ፣ በአሁኑ ጊዜ እስያ ውስጥ በኤኮኖሚ 3ኛይቱ ኀያል ሀገር መሆኗ የታወቀ ነው።

አውሮፓ የሕንድ ዋና የንግድ ተባባሪ ጀርመን ናት ። ሃቻምና በሁለቱ መካከል የ 16,08 ቢሊዮን ዩውሮ ዋጋ ያለው የንግድ ልውውጥ አድርገዋል። በጀርመን የ 2 ቀናት ጉብኝታቸውን ትናንት ያጠናቀቁት ጠ/ሚንስትር ሞዲ፣ «ሕንድ ከጀርመን የምትቀስመው ብዙ ነገር አለ» ማለታቸው ተወስቷል።

ሰውን ከሞላ ጎደል ተክተው የሰውን ተግባር የሚያከናውኑ «ማሺኖች» (ሮቦቶች )ተግባር ይበልጥ እየተሻሻለና እየተራቀቀም መምጣቱን በሰሞኑ የሃኖፈር የኢንዱስትሪ ትርዒት ላይ በመታየት ላይ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የሳይንስ ልብ ወለድ የሚመስለው ሐኖፈር ላይ ገሐድ ሆኖ እየታየ ነው። ከትንንት በስቲያ ፤ በጀርመን መራኂተ መንግሥት አንንጌላ ሜርክልና የህንድ ጠ/ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ተመርቆ የተከፈተው ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ዐውደ ርእይ፣ ሰውና ሮቦት በመጣመር ላቅ ያለ አመርቂ ውጤት ሊያስመዘግቡ የሚችሉበትን ሁኔታ ያመላከተ ነው። ማሺኖች፤ ሁሉንም ነገር የሚያከናውኑ ከሆኑ ሰው ምን ሊሠራ ነው? የሚለው ጥያቄ ራሱን የቻለ ሌላ አነጋጋሪ ጉዳይ ነው።

የግል ኮምፒዩተርን አገልግሎት የሚያውቅ ያውቀዋል። ከኮምፒዩተር ጋር አታሚ መሣሪያም ሆነ ሌላ ፤ የኤሌክትሪክ ገመድ በመሠካት ማገናኘት የተለመደ ነው። «ይሠኩና ከምፒተርዎ ሥራ እንዲጀምር ያድርጉ!»(Plug and Play! ) ብቻ ሳይሆን ፣ በዘንድሮው የሃኖፈር የኢንዱስትሪ ዐውደ ርእይ የተለመደው መሪ ቃል «ይሠኩና ኮምፒተርዎ እንዲያመርት ያብቁት !» ( Plug and Produce ) የሚል ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የተለያዩ ምርቶችን የሚያቀርቡ ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ፣ ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው ተግባራቸው በኮምፒዩተር የተቀነባበረ ነው ። ከፋብሪካው እስከምርቱ ዓይነትና የመጨረሻ ውጤቱ፤ መርኀ ግብሩን ተከትሎ የሚከናወን ነው። ለምሳሌ ያህል ከጀርመን ታዋቂ ኩባንያዎች መካከል አንዱ «ዚመንስ» በዚህ ረገድ የሚያከናውነውን መጥቀስ ይቻላል። የዚሁ ኩባንያ ባልደረባ ካርላልሃይንትዝ ካውል---

Hannover Messe Highlights 2015 Kochroboter
ምስል Reuters/W. Rattay

«ሁሉም ባጠቃላይ በራሱ በዚመንስ ሶፍትዌር ተጠንስሶ የተቀነባበረ ነው። ምርቱ ፣ ዕቃው ወይም የፋብሪካው የመጨረሻ ውጤት ፣ በአንድ የዚመንስ ሶፍትዌር ታቅዶ ከመቅድም ተግባር እስከፍጻሜ የሚከናወን ፤ ወደሌሎችም የራሱ ሶፍትዌሮች የሚሠራጭ መርኀ ግብር ነው። የተለያዩ የሶፍትዌር ዓይነቶች በዚሁ መርኀ ግብር የተሣሰሩበት ሁኔታ ተግባሩን ባጭር ጊዜ ውስጥ ማከናወን የሚያስችል ነው። ባለፉት ጊዜያት የተለያዩት የኩባናያው ሶፍትዌሮች የየራሳቸው መርኀ ግብር ነበራቸው። ወደፊት አዲሱ «የትብብር መድረክ » የተሰኘው ፤ ሁሉም የፋብሪካው ተግባር የሚቀናጅበት ክፍል «የቡድን ማዕከል » የሚል ሥያሜ ሆናል የተሰጠው። ከመጀመሪያ ሁሉም መረጃዎች ፣ ከውጥን እስከፍጻሜ በሶፍትዌሮች ቅንጅት በኩል ይተላለፋል። ሥራውም ጥራቱን የጠበቀና የተቀላጠፈ ይሆናል።»

በዘንድሮው የሐኖፈር የኢንዱስትሪ ትርዒት ፤ እንኳን ደህና መጡ ! በማለት የእጅ ሰላምታ ከሚያቀርበው ሰው መሰል ማሺን አንስቶ ፣ ከ 25 እስከ 300 ኪሎግራም ዕቃ የሚያነሱ የሚጭኑ የሚሸከሙ ሮቦቶች ለዐውደ ርእይ ቀርበዋል።

ለምሳሌ ያህል ፤ ጀርመን ውስጥ በካርልስሩኸ የቴክኖሎጂ ተቋም የሠራው FIFI የተሰኘው ሮቦት፤ በሰውና በማሺን መካከል የሚደረገውን የተቀናጀ አሠራር ፤ የ 4ኛው ኢንዱስትሪ ምዕራፍ የተሣካ እንደሚሆን ካመላከቱት የፈጠራ ውጤቶች አንዱ እንደሆነ ተነግሮለታል። በ 3 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተስተካክሎ የተሠራው FIFI ፣ የፈጣን ሯጭ፣ ጠንካራ ዕቃ ተሸካሚ ና ዐራጋፊ ጎረምሣ ተተኪ ማሺን ነው ማለት ይቻላል። ስለሮቦቶች ተግባር ከተወሳ ከሰሞኑ ፤

ጃፓን ውስጥ ፤ ከ 4 ዓመት በፊት ፤ እ ጎ አ መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ ም፤ በአደገኛ የውቅያኖስ ማዕበል (ሱናሚ) ሳቢያ ፣ ፉኩሺማ በተሰኘው የጠረፍ አካባቢ በተተተከለው የአቶም ኃይል ማመንጫ አውታር ላይ ብርቱ ፍንዳታ አጋጥሞ እንደነበረና ከዚያን ጊዜ አንስቶ አውታሩ እንደገና ሥራውን እንዳያንቀሳቅስ ታግዶ መቆየቱ የሚታወስ ነው። ያም ሆኖ የኩባንያው ባለቤቶች ሥራውን እንደገና ለማስጀመር ካላቸው ጉጉት በመነሣት ፤ በቅድሚያ በተቃጠለው አውታር ፣ የቀለጠውን የአቶም ማብላሊያ ማገዶ ፣ የአደገኛ ነጽብራቁንም ይዞታ ፣ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እንዲመረምርና መረጃ እንዲያቀርብ ያሠማሩት ሰው -መሰል ሮቦት ነበር። ሮቦቱ፣ 2/3ኛውን የተለያየ ተግባር ካከናወነ በኋላ፣ በመጨረሻ ስለወደቀ ሥራው ተቋርጧል ነው የተባለው። ሮቦቱ፤ እንደለካው ከሆነ በአውታሩ አዘቅት ውስጥ የአደገኛው የአቶም ጨረር መጠን እስከ 9,7 Sievert ይደርሳል። ይህም በአንድ ሰዓት ውስጥ ሰውን የሚገድል አደገኛ ጨረር ነው።

Hannover Messe Highlights 2015
ምስል Deutsche Messe AG/R. Jensen

አሁንኑ ዘመን፤ መላው ዓለም፣ 4ኛ ስለተሰኘው የኢንዱስትሪ አብዮት ሆኗል የሚነጋገረው። ስለኢንተርኔትና ዓለም በዲጂታል ስለተሣሠረችበት ሥነ -ቴክኒክ! የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ አብዮት በውሃ እንፋሎት ተሽከርካሪን ለምሳሌ ያህል ባቡርን ማንቀሳቀስ የተቻለበት ርምጃ ሲሆን፣ ሁለተኛው የኤልክትሪክ ጠቀሜታ ፤ ከዚያም በኋላ ነው ኮምፒዩተር የሚከተለው። እነዚህ ሁሉ አሁን ዓለም ለደረሰበት ፈጣን መገናኛና መገልገያ ታላቅ እመርታ ነው ያስገኙት።

በዚህ የኢንዱስትሪ አብዮት አሁን ማነው የመሪነቱን ቦታ የያዘው ለሚለው ጥያቄ በማሺን አቅርቦት ፤ በአውታሮጭ ተከላና በመሳሰለው የታወqq,ው የአንድ ጀርመናዊ ቤተሰብ ኢንዱስትሪ ኩባናያ የሆነው የቦርድ ሊቀመንበር ፊሊፕ ሃርቲንግ እንዲህ ብለዋል።

«እንደኔ እይታ፤ በውድድሩ ገና ጎልቶ የወጣ አሸናፊም ሆነ ትንሽ ቀደም ብሎ የተገኘ የለም።

አሜሪካውያን በሶፍትዌር ረገድ በጣም ጥሩ ናቸው። እንዲሁም በመረጃ ቴክኖሎጂ! ጀርመናውያን ፤ በፋባሪካ ምርትና በአውቶማቲክ የኢንዱስትሪ ተግባር በጣም ጥሩ ናቸው። ካምናውጋ በዚህ ረገድ ሳነጻጽር፣ ጀርመን ትልቅ እመርታ አሳይታለች። ይህም ማለት «ኢንዱስትሪ 4» የሚሣካ ነው። ሥራ ላይ የሚውልበት አካሄድ ውጤትም ላይ የሚደረስበት ተጨባጭነት ያለው ነው። ከአንድ ዓመት በፊት እነዚህን ምልክቶች በግልጽ ማየትም ሆነ ማገናዘብ የሚቻል አlkeነበረም። በሌሎች ኢንዱስትሪi ኩባንያዎችም ተመሳሳይ ሁኔታ አለ።»

ከኢንዱስትሪው 4ኛ ምዕራፍ ለመድረስ የታየው እመርታ፣ የምርትን ጥራት ከፍተኛ ዓለም አቀ ፋዊ ደረጃ ለማሰጠት ሲሆን፤ የአዲሱ ደረጃ አመዳደብ ከተጀመረ ቆይቷል።

ለኢንዱስትሪ ዕድገትና ልማት፤ የሰውና የማሺን ቅንጅት በታየበት የሃኖፈሩ የኢንዱስትሪ ዐውደ ርእይ፣ ሌላው አነጋጋሪና አሳሳቢ ጉዳይ በሰው ሠራሽ ጥበብ ፤ ድካም የማያውቁ መዓልትና ሌሊት የሚሠማሩ የማሺን ወታደሮችሥምሪት ነው። ማሺኖቹ በራሳቸው ውሳኔ እንዲዋጉ የሚደረግበት ሁኔታ በ 5 እና 10 ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል መባሉ አስደንጋጭ ነው። እንደ አንዳንድ የኑክልየርና በጅምላ ሕዝብ ጨራሽ የሆኑ ጦር መሣሪያዎች ይህም የሚታገድበት (የሚከለከልበት) ሁኔታም ሆነ ውል ካልተደረገ የጥፋቱን መጠን ለማሰብ ይከብዳል!

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ