1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ወደ መኢአድ መሪነት መመለስ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 18 2003

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ቅዳሜ እና ዕሁድ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከፖለቲካው ዓለም ራሳቸውን እንዳገለሉ የተናገሩትን የድርጅቱን ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውልን በድጋሚ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ድርጅቱን እንዲመሩ መርጧል ።

https://p.dw.com/p/QkTG
ኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ይህን የፓርቲውን ከፍተኛ ሥልጣን ለሌላ ያስረክባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር ። ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ ሌላ ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር መኢአድ ለመዋሀድ የጀመረው ድርድር ተግባራዊ እንዲሆንም በሙሉ ድምፅ ወመሰኑን የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሰ ዕንግዳው ዘግቧል ። ታደሰ ዕንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሀመድ