1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢድ አልአድሀ አከባበር በአዲስ አበባ እና በሳዉዲ

ዓርብ፣ ነሐሴ 26 2009

አንድ ሺህ አራት መቶ ሠላሳ ሥምንተኛዉ የኢድ አልአድሀ በዓል በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ለሐጂ ሃይማኖታዊ ጉዞና ፀሎት ወደ መካ ሳዉድ አረቢያ ከሁለት ሚሊየን የሚበልጡ ተሳላሚዎች መጓዛቸዉ ተነግሯል። እዚያም በተደረገዉ ከፍተኛ የፀጥታ የበዓሉ ሥርዓት በጥንቃቄና እርጋታ መከናወኑን ዘገባዎች ያስረዳሉ።

https://p.dw.com/p/2jE7B
Äthiopien Addis Abeba | Opferfest Eid al Adha
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የኢድ አልአድሀ አከባበር በአዲስ አበባ

 በዘንድሮዉ የሐጂ ሃይማኖታዊ ጉዞ እና ጸሎት ወደ ሰባት ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን መሳተፋቸዉን ጄዳ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለዶቼ ቬለ ገልጿል። በዓሉን በዚያዉ ሳዉድ አረቢያ የሚያከብሩ ኢትዮጵያዉያን ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት የሳዉዲ መንግሥት በዉጭ ዜጎች ላይ የጣለዉ የነፍስ ወከፍ ግብር፣ የትምህርት ቤት ክፍያ እና ሌሎች ወጪዎች የበዓል ድባባቸዉ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፏል። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በውጭ ሀገር ዜጎች እና በቤተሰቦቻቸው ላይ በጣለው የነፍስ ወከፍ ክፍያ የተነሳ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን ልጆቻቸውን ወደ ሀገራቸዉ እየላኩ ነው፡፡  ይሁንና የኑሮን ውጣ ውረዱን ተቋቁሞ በዓሉን በተረጋጋ መንፈስ ማክበር እንደሚያስፈልግ አንድ የሃይማኖት አባት መክረዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም። ኢትዮጵያ ዉስጥም በተለይ በአዲስ አበባ ስታድዮም ፀጥታዉ በተጠበቀ መልኩ በዓሉ ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙ የሃይማኖቱ መሪዎች እና የመንግሥት ኃላፊዎች በሀገሪቱ የመቻቻል ባህል እንዲጎለብት ጥሪ አቅርበዋል።

Haddsch Islamische Pilgerfahrt nach Mekka | Saudi-Arabien, Mekka
ምስል picture-alliance/Anadolu Agency/F. Yurdakul

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር/ነብዩ ሲራክ/ ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ