1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራና ሱዳን ስደተኞች እጣ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2005

ባለፈዉ ሳምንት ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በአንድ ትልቅ አሮጌ ጀልባ ተሳፍረዉ ወደሞልታ ደሴት ሲቃረቡ ጀልባዉ ተበላሽቶ ከመቶ በላይ ስደተኞች ነፍሳቸዉን የሚታደግ እስኪያገኙ ባህር ላይ ለቀናት ሲጨነቁ ቆይተዋል።

https://p.dw.com/p/19Q4f
ምስል picture-alliance/dpa

የሜዲትራኒያን ባህርን አቋርጠዉ ወደአዉሮጳ ለመዝለቅ የሞከሩት አራት ነፍሰጡሮች፤ የአምስት ወር ጨቅላ ሕጻንና አንድ የቆሰለ ሰዉን ጨምሮ አንድ መቶ ሁለት ስደተኞችን የጫነችዉን አሮጌ ጀልባ የሞልታ መንግስት ወደመጣችበት ለመመለስ ሲወስን የጣሊያን መንግስት በተቃራኒዉ ወደግዛቱ እንዲገቡ አድርጓል። የስደተኞቹን ነፍስ የታደገችዉ በአንድ የግሪክ መርከበኛ የምትመራ ሰላሚስ የተሰኘች መርከብ መሆኗን የሮሙ ወኪላችን ተኽለእዝጊ ገብረኢየሱስ በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። አሁን ስደተኞቹ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ቀጣይ እጣፈንታቸዉስ፤ ተኽለእዝሂ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ተኽለእዝጊ ገብረኢየሱስ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ