1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራዉያን ቀረጥና ስዊድን

ሐሙስ፣ የካቲት 29 2004

የስዊድን ምክር ቤት በሐገሪቱ የሚገኙ የኤርትራ ተወላጆች ለአስመራ መንግስት የሚልኩትን ሁለት በመቶ ቀረጥ ለማስቆም ተወያየ። ምክር ቤቱ ስዊድን የሚገኙ ኤርትራዉያን የተጠቀሰዉን ቀረጥ ለትዉልድ ሐገራቸዉ መንግስት የሚከፍሉት ተገደዉ እንደሆነና

https://p.dw.com/p/14HNo
አስመራ ከተማምስል picture-alliance/ dpa

እንዳልሆነም ፖሊስ እንዲያጣራም ጠይቋል። ጉዳዩ ስዊድን ምክር ቤት የቀረበዉ ሁለት በመቶዉን ቀረጥ ለኤርትራ መንግስት መላክን በሚቃወሙ ኤርትራዉያን ጠቋሚነት ነዉ። ርምጃዉ ኤርትራ ያሰረችዉን የስዊድን ዜግነት የያዘ ትዉልደ ኤትርትራዊ ጋዜጠኛ ለማስለቀቅ ከሚደረገዉ ጫና አንዱ ነዉ የሚለዉን ግምት ግን የስዊድን ማዕከላዊ ፓርቲ የፍትህ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ዮሃን ሊናንዶር አስተባብለዋል።

«ኤርትራ ዉስጥ የማይኖሩ ስዊድን የሚገኙ የኤርትራ ተወላጆች ቀረጥ መክፈላቸዉን በሚመለከት ከተለያዩ የምክር ቤታችን አባላት ሃሳቦች ቀርበዋል። ይህንን አስተያየትም ባለፈዉ ሳምንት በምክር ቤታችን አስተናግደናል፤ አሁን የፖሊስ ምርመራ እየተካሄደ ነዉ፤ ይህን የሚቃወሙ አንዳንድ ኤርትራዉያን ጉዳዩ በፖሊስ እንደሚረመር ስለጠየቁ፤ ያ እየተደገ ነዉ፤ ለጊዜዉ የፖሊስ የምርመራ ተግባር ተጠናቆ ከስዊድን ህግ ተፃራሪ ስራ መከናወኑን እስኪያጣራ ከምክር ቤቱ የምናደርገዉ አይኖርም።»

ዮሃን ሊናንዶር የስዊድን ማዕከላዊ ፓርቲ የፍትህ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ናቸዉ። እናም እሳቸዉ እንደሚሉት የፖሊስ ምርመራ ኤርትራዉያኑ ተገደዉ ለትዉልድ ሐገራቸዉ መንግስት ሁለት በመቶ ቀረጥ መክፈላቸዉን ካረጋገጠ ምክር ቤታቸዉ በአንፃሩ ርምጃ ሊወስድ ይገደዳል። እንዲያም ሆኖ ስዊድን የሚኖሩ ኤርትራዉያን በዚህ ረገድ ያላቸዉ አቋም መለያየቱንም ሊናንዶር ይገልፃሉ፤

Flash-Galerie europäische Königshäuser Schweden Schloss Drottningholm
የስቶክሆልም ቤተመንግስትምስል picture alliance/Arco Images

«እዚህ መኖር የጀመሩ አንዳንድ ከኤርትራ የመጡ ሰዎች ይህን በፈቃደንነት ነዉ የምንከፍለዉ ይሉናል፤ በተቃራኒዉ እንዲህ ያለዉን ቀረጥ የማይፈልጉ አንዳንዶች የብቀላ ርምጃ ፍራቻ አላቸዉ፤ ካልከፈሉ ምናልባት አገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻቸዉ ይታሰሩብናል እና የመሳሰለዉ።»

የተመድ ኤርትራ ዉጭ ሐገሮች ከሚኖሩ ዜጎቿ ጠቀም ያለ የዉጭ ምንዛሪ እንደምታገኝ መጥቀሱ ይታወሳል። ስለሚሰበሰብበት መንገድ ግን በይፋ የተባለ ነገር የለም። ስዊድን ከሚገኙ የኤርትራ ተወላጆች ሁለት በመቶዉ ቀረጥ የሚሰበሰብበት ስልት ይታወቅ እንደሁ ለቀረበላቸዉ ጥያቄ ዮሃን ሊናንዶር ይህን ብለዋል፤

«እንደ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት አገላለጽ ከሆነ ኤምባሲ ዉስጥ በሚሠሩ ሰዎች አማካኝነት ነዉ። ከእነዚህ ሰዎች አንዳንዶቹ ዲፕሎማሲያዊ ያለመከሰስ መብት አላቸዉ፤ በዚህ ምክንያት ምናልባት የስዊድን ባለስልጣናት ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ላይኖር ይችላል። ሆኖም አንዳንድ በፖሊስ ምርመራ ሥር ያሉ እዚህ የሚኖሩ ሰዎች አሉ እነሱ ግን ያዉ በስዊድን ህግ ሥር የሚገኙ በመሆናቸዉ ወንጀል ፈፅመዉ ከተገኙ ክስ ሊመሰረትባቸዉና ርምጃም ሊወሰድ ይችላል።»

ስዊድን ዉስጥ የሚኖሩ ኤርትራዉያን ለቤተሰቦቻቸዉ ባሻቸዉ ጊዜ ገንዘብ መላክ እንደሚችሉ የገለፁት የስዊድን ማዕከላዊ ፓርቲ የፍትህ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ዮሃን ሊናንዶር የመንግስታቸዉ ተቃዉሞ ሌላ ሐገር በስደት ከሚኖር ዜጋ በግዴታ የማይገናኝ ቀረጥ መሰብሰብን እንደሆነም በአፅንኦት ገልፀዋል። ይህ የስዊድን ምክር ቤት ርምጃ የኤርትራ መንግስት ካለክስ ያሰረዉን የስዊድን ዜግነት ያለዉ ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሃቅን ለማስለቀቅ የሚሞክር ጫና ነዉ የሚሉ ዘገቦችን ግን ሊናንዶር አስተባብለዋል፤

Blick über die Häuser von Asmara, Independence Avenue
ምስል picture-alliance/ dpa

«በፍፁም ይህን ጉዳይ በምክር ቤቱ ዉይይታችን አላነሳንም። ከዚህ ጋ የሚያገናኘዉ ነገር ምንም የለም።»

የተመድም የኤርትራ መንግስት ላይ ተመሳሳይ ጫና ለማሳረፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይታወቃልና ስዊድንም በበኩሏ ይንኑ ግፊት ልታንር ይሆን? ዮሃን ሊናንዶር፤

«ይህ የኤርትራን መንግስት መፃረር አይደለም። እኛ የፈለግነዉ ስዊድን ለሚኖሩ ሰዎች፤ የስዊድን ህግ ለሁሉም እኩል ነዉ፤ ከሐገራቸዉ መጥተዉ ስዊድን የሚኖሩ የየትኛዉ ሐገር ዜጎች ሳይፈልጉ እንዲህ ባለዉ ቀረጥ ስም እንዲዘረፉ እንፈልግም። ያንን በመቃወም ነዉ ርምጃ መዉሰድ የፈለግነዉ። ይህ ፍትሃዊ ነዉ ብለን አናስብም፤ የሚኖሩት ስዊድን በመሆኑ ለስዊድን ቀረጥ ይከፍላሉ፤ ለትምህርት ቤት፤ ለጤና አገልግሎት ለሌላ ሌላም ይከፍላሉ፤ በዚያ ላይ ደግሞ ተገደዉ ተጨማሪ ገንዘብ መክፈል የለባቸዉም።»

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ