1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤድስ ስርጭትና መድኃኒት ማከፋፈል በኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ሐምሌ 19 2002

ኤች አይ ቪ በደማቸው ውስጥ ያለ ሰዎች በብዛት ከሚገኙባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት ። ይሁንና በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ የኤድስ በሽታን በሚያስከትለው ቫይረስ የሚያዙ አዋቂዎች ቁጥር ከቀደሙት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር መቀነሱን የመስኩ ባለሞያዎች ያስረዳሉ ።

https://p.dw.com/p/OUym
ምስል picture-alliance/dpa

እንደ ባለሞያዎቹ አገላለፅ ከሰሀራ በታች ከሚገኙ ሌሎች የአፍሪቃ አገራት ጋር ሲወዳደርም በኢትዮጵያ አዳዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እየወረደ መጥቷል ። የፀረ ኤች አይ ቪ መድኃኒት ስርጭትም ከቀድሞው በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል ። ሆኖም ካቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ሰዎች እንደሚሉት የተጓዳኝ በሽታዎች ህክምና አለመሟላት አንዱ ዓብይ ችግራቸው ነው ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ