1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእሥራኤልና የሐማስ ፍልሚያ እንዲቆም የተያዘው ዓለም አቀፍ ምክክር

ሰኞ፣ ሐምሌ 7 2006

በእሥራኤልና በጋዛው የፍልስጤማውያን ኃይል ፣ ሐማስ መካከል፣ በአየር ኃይል ድብደባና በሮኬት አጸፋዊ መልስ በተለይ በጋዛ የብዙ ሲቭሎች ሕይወት የተቀጠፈበት ፍልሚያ ከተጀመረ ሰባት ቀን ሆኖታል። ተኩስ ይቆም ዘንድ

https://p.dw.com/p/1CcrO
ምስል Reuters

የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ጥበቃው ም/ቤት ፣ በኒው ዮርክ፤ የዐረብ መንግሥታት ማሕበር በካይሮ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው። የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ፍርንክ -ቫልተር ሽታይንማየር በበኩላቸው የፍልስጤማውያኑን ፕሬዚዳንት ማሕሙድ አባስንና የአሥራኤሉን ጠ/ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን በማነጋገር የሽምግልና ጥረት እንደሚያደርጉ ተገልጿል ። ስለወቅታዊው የእሥራኤል ጋዛ ፍልሚያ ፤ የእሥራኤሉን ዘጋቢአችንen ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ግርማው አሻግሬ/ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ